May 4, 2019 : ዘ-ሐበሻ

በሚያዝያ 25/2011 የሶማሌ ክልላዊ መስተዳድር በዓፋር ክልላዊ መንግሥትና ህዝብ ላይ የጦሪነት አዋጅ ማወጁ ይታወሳል። ይህ አዋጅ ሁለት መሠረታዊ ሁኔታዎችን የዘለለ ይመሰለኛል።አንደኛዉ በሀገራችን ታሪክ ምታ ነጋሪት ክተት ሠራዊት የማለት ሥልጣን የነበረዉ ማዕከላዊ መንግሥት ሰለነበረ ቆለኛዉ የክልሉ መንግሥት ተለምዶአዊዉን ሥርዐት መዝለሉ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ የክተት አዋጅ ማሰነገር የሚችለዉ ሶማሌም የተወከለበት ፌዴራል ፓርላማ ሰለነበረ ካቢነዉ ይኸኛዉንም ህገ-መንግስታዊ አንቀፅን የዘለላት ይመሰላል። ይህ አካሄድ ህገመንግስታዊ ክፍተት ብኖርበትም እዝህ ጋ መድረሳችን ለቆለኞቹ ለጊዜውም ቢሆን ደስ ብሎናል። ብዙ ጊዜ እኛ አዋጅ የምታወጅብን የዳር ህዝቦች ነበርን እንጂ ሌላውን ለመዉጋት አዋጅ አዉጀን ጦር ሰብቀን አናዉቅም። ባይሆን የዘወትር ሥራችን በመከላከል ላይ ያመዘነ ነበር።

ሌላዉ ያሰቀየመንና አብዛኛውን የሀገሬን ሰዉ ያስገረመው ነገር ከአንድ ሳምንት በፊት በተጋበዘበት መድረክ ሰለ ኢትዮጵያዊነት እና የአንድነት ፈይዳዉ ላይ በሰጠዉ ድሰኩር ታዳሚዎችን ብቻ ሳይሆን ጎረቤት ሂዶ ኢቲቪን የሚከታተለዉን የእኔ አይነቱን በተለይ በንግግሩ ያሰደመመው ጎበዝ ያጨበጨንበት እጆቻችን ስምበራቸዉ ሳይጠፋ ወንድም በሆነዉ ቆለኛዉ ዓፋር ላይ ጦርነት ማወጁ ለካ ድሀ በአቻዉ ላይም እንድህ ክንዱ ይበረታል ማሰባሉ ከማሰተዛዘብም አልፎ ይሄ ነገር ያሸነፍከዉን ምታ ብሉት…….አሰኝቷል። በኢህአዴግ ዘመን ሥልጣን የዛፍ ላይ እንቅልፍ ነዉ እንደተባለ ሁሉ ማድነቅም እንድሁ ወረት ነው እንደ ሳያሰኝ አልቀረም። አቶ ሙሰጠፈ ይህን ያህል የፖለቲካ ብሰለት ይጎድለዋል ወይም ሶማሌዎች እንድሁ የፖለቲካ ብሰለት ይጎድላቸዋል ብየ አላምንም ነበረ። ሙሰጠፈ የፌሰቡክ አክትቪሰትና የተራድኦ ሠራተኛ እንደነበረ ባለፈዉ ጊዜ ነግሮናል። ጥሎብን ዉጪ የተማረ ወይም ዉጪ የሰራ ከተባለ የኋላ ታሪኩን እንኳ በወጉ ሳንረዳ እናደንቃለን። ከማድነቅም አልፈን ዉጪ ሀገር የሚኖር ነው ከተባለ እንጨት ፈልጠን፥ ዉሀ ቀድተን፥ ቦርዴ ሸጠን ያሳደግናትን የአብራካችን ክፋይም ብሆን ከተጠየቅን አይናችንን ሳናሸ እንሰጥና ኋላ የታሰበው ቀርቶ ያልታሰበዉ ሲመጣ ወይ ነዶ እያልን ከንፈር እንመጣለን። የክቡር ፕሬዚደንት ሙሰጠፈ አድናቂዎችም እንድሁ ነዉ የሆንነወ። ትልቁ ጥያቄ የዝህ ክተት አዋጅ ኮርኳሪ ምክንያቶች(motives) ምንድናቸዉ የሚለዉ ይመሰለኛል። ሶማሌዎች እነሱ በሰም የጠቀሷቸው ቀበሌዎች የሶማሌ ክልል አካል እንዳልሆኑ በሚገባ የሚያዉቁት ጉዳይ መሆኑ ሶማሌ ዒሳ በዓፋር ክልላዊ መንግሥት ሰር መብታቸው ተጠብቆ እንዲኖሩ ብለዉ ስምምነታቸውን በፊርማቸው ማኖራቸዉ ዋነኛዉ ምሰክር ነዉ። ዛሬ ፈረሴን ከአዋሸ ወንዝ ዉሀ ሳላጠጣ ከተመለሰኩ ወላዲተ አምላክ አትማረኝ ብሎ ለያዥ ያስቸገረው ምክትል ፕሬዝዳንቱ አደም ፋራሕ እነዝህ ቀበሌዎች የዓፋር ናቸዉ ብለው አሻራቸውን ካኖሩት ክቡራን ምሰለነዎች አንደኛው ናቸው። ታድያ ዛሬ ምን መጣ ወይም ተገኘ ነዉ በየሰዉ ጭንቅላት ውስጥ የሚመላለሰው ጥያቄ። አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች (አሁን ሁሉም ተንታኝ ሁኗል) በቅርብ ጊዜ በአዳማ ከተማ የተካሄደው የኦሮሶማ ሠላም ኮንፈረንስ በሁለቱ አጎራባች ክልሎች መካከል ከምን ጊዜም በላይ መተማመንን ሰለፈጠረ የማዕከላዊ መንግሥቱን አመራር በእጁ ያሰገባዉ ኦዲፒ ሶማሌዎች ኦሮሚያ ላይ የይገባኛል ጥያቄ እሰካላነሱና እንደ ልማዳቸዉ በንቀት እሰካልተነኮሱ ለጊዜውም ቢሆን የምህረት ጊዜ (Grace period) ይኖራቸዋል ከሚል እሳቤ የመነጨ ነው ሲሉ ሌሎች ደግሞ የኦዲፒ አመራሮች ብዙ ድንበር የምንዋሰነዉና የጎን ዉጋት የሆኑብን ሶማሌዎች ሰለሆኑ ከእነሱ ጋር የምናደርገው ዕርቅ ለጊዜውም ቢሆን ከአማራ ዲሞክራቲክ ፓርቲ ጋር ለሚኖረን ዉሰጠ ድርጅት ፍትጊያ ይጠቅመናል ብለዉ ሰላመኑ ሶማሌዎች በአሁኑ ጊዜ የሚፈፀሙት ማንኛውንም ድርጊትን ቀድመው እንደማይቃወሙ መተማመኛ ሰለሰጡ ነዉ ይላሉ።

ራቅ ያሉት ደግሞ ዓፋሮች ብዙ ጉርብትናቸዉና ዉግንነታቸዉ ለአማራ ሰለሆነ አለፍ ሲልም ለትግራይ ሰለሆነ ከአማራ ወይም ከትግራይ ጋር ለምናደርገው የሥልጣን ፍትጊያ የሶማሌዎችን ያህል ሰለማይጠቅሙን ለጊዜው ለአፋሮች የነበረን ዉግንናን ለዘብ እናድርገው ብለዉ ኦሮሞዎች ሰለመወሰናቸው ሙሰጠፌ ሚሰጥር ሰላገኘ የልብ ልብ አግኝቶ ነው ይላሉ። ማንም ምን ይበል ማንም ምን ይወሰን ዛሬ በዓፋር ህዝብ ላይ የታወጀው ጦርነት ለሀገራችን ሰላምና ማዕከላዊ አንድነት የሚሰጠው አንደምታ በሚገባ መጤን አለበት። ሙሰጠፌ ሞቃዲሾ እንዳሉት የጦር አበጋዞች በነሸጠዉ ቁጥር ጎረቤቶቹን ሰወር ነግ በነ ተብሎ እርምጃ እሰካልተወሰደ ሀገረ ኢትዮጵያ ወደ ዘመነ መሳፍንት መመለሷ ነው።

ሶማሊያ በ1960ዎቹ ነፃ ወጥታ እንደ ሀገር ከተመሰረተች ጊዜ ጀምሮ ትልቋ አጀንዳ ዓፋሮችን አጥፍቶ ድንበሯን አዋሸ ወንዝ ድረሰ መዘርጋት ሰለነበረ የአሁኑ የሙሰጠፌ ክተት አዋጅ ለአፋሮች አዲሰ ስላልሆነ እንዳመጣጡ የሚሰተናገድ ሲሆን ማንም ሠላም ወዳድ ኢትዮጵያዊ ከጎናችን ይቆማል ብለን ስናምን የአሰብ አዲስ አበባ አውራ ጎዳና በዚያድ ባሬ እጅ መዉደቅ ጦሱ ለአፋር ብቻ እንዳልሆነ ታዉቆ ሙሰጠፌን አይዞህ ያለዉን አካል አብረን እናውግዝ እላለሁ።

አካዳር ኢብራሂም