May 4, 2019

ሰሜን ሸዋ ዞን ምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ግጭት ተቀስቅሷል፤ የሁለት ሰዎች ሕይወት አልፏል፤ የቆሰሉ ሰዎችም አሉ።የመከላከያ ሠራዊት 8:00 አካባቢ በቦታው ደርሷል፤ ነገር ግን ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ በመኖሩ ወደ ማረጋጋት መግባት አልቻለም።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ይትባረክ አብርሃም ለአብመድ እንደገለፁት በአካባቢው በግጦሽ መሬት ምክንያት ግጭት በተደጋጋሚ ይከሰታል፤ አሁን እየተከሰቱ ላሉት ግጭቶች ምክንያቶች ግን ከዚህ የተለዩ መሆናቸውን ነው የተናገሩት።

አብመድ