May 5, 2019

Source : https://mereja.com/amharic/v2/114365

አንዳንድ የክልል አመራሮች ፖለቲካዊ ፍላጎታቸውን አስገድደው ለማስፈጸም ተፈናቃዮችን በካምፖች እስከ ማገት መድረሳቸው ተገለጸ
Reporter Amharic

Image result for muferiat kemal

‹‹እንደ ዜጋም እንደ አመራርም ግራ የሚያጋቡኝ ሁኔታዎች አሉ››
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን
 ‹‹ጨከን ማለትና መከፈል ያለበት ተከፍሎ የዜጎችን ሥቃይ ለማስቆም ወስነናል››
 ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል

አንዳንድ የክልል አመራሮች ፖለቲካዊ ፍላጎታቸው እንዲፈጸምላቸው ጫና ለመፍጠርና ለማስገደድ ተፈናቃዮችን በካምፖች እስከ ማገት የደረሰ ተግባር እየፈጸሙ እንደሚገኝ የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ለፓርላማ ገለጹ።
ሚኒስትሯ ይህንን የተናገሩት በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በተፈጠሩ ግጭቶች ከቀዬያቸው የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ያሉበትን ሁኔታ በአካል ተገኝቶ እንዲገመግም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከሁሉም የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴዎች የተወጣጡ አባላትን በማካተት ያዋቀረው የሱፐርቪዥን ቡድን፣ የምልከታ ሪፖርቱን ዓርብ ሚያዚያ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ለምክር ቤቱ ልዩ ስብሰባ ባቀረበበት ወቅት ነው። በአጠቃላይ የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ጉዳይና ፓርላማው ያሰማራው የሱፐርቪዥን ቡድን ያቀረበውን ሪፖርት በተመለከተ ማብራሪያ ለመስጠት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የሰላም ሚኒስትሯወ/ሮሙፈሪያት ካሚል፣ የትምህርት ሚኒስትሩ ጥላዬ ጌጤ (ዶ/ር) እና ሌሎች ጉዳዩ የሚመለከታቸው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተው ነበር።
በአገሪቱየተለያዩአካባቢዎችበተፈጠሩግጭቶችየበርካታዜጎችሕይወትመጥፋት፣የአካልጉዳት፣ከመኖሪያቀዬአቸው የመፈናቀልአደጋበዜጎችላይእንዳጋጠመየሱፐርቪዥንቡድኑባቀረበውሪፖርትገልጿል፡፡ቡድኑባሰባሰበውመረጃመሠረትበትግራይክልል 111,465፣በደቡብክልል 873,272፣በኦሮሚያክልል 1.4 ሚሊዮንበላይ፣ እንዲሁምበአማራከ107 ሺሕበላይየተፈናቀሉዜጎችበመጠለያካምፖችእንደሚገኙአስረድቷል።
ለተፈናቃዮቹየተለያዩሰብዓዊድጋፎችየማድረግናመልሶየማቋቋምሥራበተወሰነደረጃየተሠራቢሆንም፣በቂእንዳልሆነናተፈናቃዮቹበአስቸጋሪሁኔታውስጥእንደሚገኙቡድኑበሪፖርቱአመላክቷል።
የቀረበውንሪፖርትከሞላጎደልሙሉበሙሉየተቀበሉትወ/ሮሙፈሪያት፣በግጭቶችምክንያትነዋሪዎችንከቀዬአቸውየማፈናቀልየወንጀልከ2008 ዓ.ም.ጀምሮየተቀሰቀሰናያልተቀረፈችግርእንጂ፣ዘንድሮየመጣእንዳልሆነግንዛቤእንዲወሰድአሳስበዋል።
በመንግሥትመዋቅርውስጥያሉየፖለቲካአመራሮችየችግሮቹጠንሳሽናአቀጣጣይ፣እንዲሁምእንዳይፈታእክልበመፍጠርበዋነኝነትተሳታፊበመሆናቸውችግሩንበአጭርጊዜውስጥመፍታትምሆነማስቆምእንዳልተቻለገልጸዋል።
‹‹አንዳንድ አካባቢ የፖለቲካ አመራሩ ራሱ ገዳይ ወይም አስገዳይ ሆኖ በሌላ በኩል ደግሞ የመብት ተቆርቋሪ ሆኖ ይቀርባል፤›› ያሉት ሚኒስትሯ፣ እነዚህን ኃይሎች በሕግ ቁጥጥር ሥር ማዋል ካልተቻለ ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ እንደማይቻል ጠቁመዋል።
‹‹በአንዳንድክልሎችያሉአመራሮችተፈናቃዮችን “ሆስቴጅ” (ማገት) የማድረግተግባርእየተፈጸመነው።ይህካልተሟላልኝተፈናቃዮችንወደቀዬአቸውእንዲመለሱአላደርግምየሚልአመራርአለ።የወሰንጥያቄዬካልተመለሰተፈናቃዮችንአልመልስምየሚልአመራርአለ፤›› ብለዋል።
በተጨማሪምበአንዳንድክልሎችነዋሪዎችንበማፈናቀልድርሻየነበራቸውተጠርጣሪዎችን፣በሕግቁጥጥርሥርእንዳይውሉየመንግሥትመዋቅሩከለላእንደሚያደርግናአሳልፎአለመስጠትመኖሩንምገልጸዋል።
ለአብነትምበጉጂና በጌዴኦአካባቢዎችሕግየማስከበርሥራገናአልተነካምያሉትሚኒስትሯ፣በዚህአካባቢበተቀሰቀሰግጭትናዜጎችንየማፈናቀልወንጀልተጠርጥረውከሚፈለጉትውስጥዘጠኙብቻበቁጥጥርሥርመዋላቸውንአስረድተዋል፡፡
በሌላበኩልበቤንሻንጉልጉምዝክልልከሚፈለጉት 183 ተጠርጣሪዎችመካከል፣በቁጥጥርሥርያልዋሉትስድስትብቻ መሆናቸውንFiled in:Amharic