Author: ኢትዮ ኦንላይን

2019-05-08

ንቅናቄው ዛሬ ባደረገው መደበኛ ጉባኤ ወደ አዲስ የፖለቲካ ተቋምነት የሚያደርገውን ጉዞ ለማሳካት በ243 የድጋፍ ድምፅ እና በ18 የተቃውሞ ድምፅ በ14 ድምፀ ተዓቅቦ ንቅናቄው በይፋ ራሱን አክስሟል።

ጉባኤው በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ለመወሰን ውይይቱን ቀጥሏል።

የቀድሞው አንድነት ፓርቲ አመራሮችና አባላት፣ ሰማያዊ ፓርቲ፣ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ እና ሌሎች አራት የፖለቲካ ተቋማት በጋራ የሚፈጥሩት ህብረ ብሔራዊ የፖለቲካ ተቋም ይጠበቃል።