የጌድዮ ተፈናቃዮች
አጭር የምስል መግለጫ የጌድዮ ተፈናቃዮች

በዓለማችን በአንድ ዓመት ውስጥ ከመኖሪያ ቀያቸው የተፈናቀሉ ሰዎች ቁጥር 41 ሚሊየን መድረሱን አንድ ሪፖርት አመለከተ።

‘ግሎባል ሪፖርት ኦን ኢንተርናል ዲስፕለስመንት’ የተሰኘው ሪፖርት እንደጠቆመው፤ በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት የተነሱ ግጭቶች የተፈናቃይ ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር አድርገዋል።

በችግር ላይ የሚገኙት ተፈናቃዮች

የሀገር ውስጥ መፈናቀል ላይ ያተኮረው ይህ መረጃ እንደሚያሳየው፤ ከዚህ ቀደም ዓለም ላይ ይህን ያህል ቁጥር ያላቸው ሰዎች ተፈናቅለው አያውቁም።

በሪፖርቱ መሰረት፤ ባለፈው ዓመት ብቻ 28 ሚሊየን ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸውን ወደሌላ የሀገራቸው ክፍል ተሰደዋል። የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ቁጥር እአአ ከ2017 መጨረሻ በአንድ ሚሊዮን ሲጨምር፤ ከአጠቃላይ የዓለማችን ስደተኞች ቁጥር ደግሞ በሦስት ሁለተኛ ብልጫ አሳይቷል።

የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ተፈናቃዮች ለችግር ተዳረግን አሉ

ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ካሉባቸው ሀገራት መካከል ለዓመታት ግጭት የነበረባቸው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ሶሪያ ቀዳሚዎቹ ሀገራት ናቸው።

ኢትዮጵያም በቅርቡ በተከሰቱ ብሔር ተኮር ግጭቶች ሳቢያ ከፍተኛ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ካሉባቸው ሀገራት ዝርዝር የገባች ሲሆን፤ ባለፈው ዓመት ወደ ሶስት ሚሊየን የሚጠጉ ዜጎች ከቀያቸው ተፈናቅለዋል።

የሞያሌ ተፈናቃዮች ያሉበት አሳሳቢ ሁኔታ

ጎርፍ፣ ሰደድ እሳትና ድርቅን የመሳሰሉት ተፈጥሯዊ ክስተቶች በቻይና፣ በሕንድ፣ በፊሊፒንስና በአሜሪካ ለሚሊየን ሰዎች መፈናቀል ምክንያት ሆነዋል።

በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሰክሬታሪያት የሆኑት ቢልለኔ ስዩም ትናንት መግለጫ በሰጡበት ወቅት፤ ከግለሰቦች መፈናቀል ጀርባ ካሉ ተጠርጣሪዎች 1300 በቁጥጥር ሥር ውለዋል ብለው ነበር።

ፕሬስ ሴክረተሪዋ በመግለጫቸው፤ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እየተመለሱ እንደሆነና፤ እስካሁን 875ሺህ ሰዎች ይኖሩበት ወደነበሩበት አካባቢ እንደተመለሱ አሳውቀዋል።

የተጠበቀውን ያህል የቤንሻንጉል ተፈናቃዮች አልተመለሱም

ተፈናቃዮች ፍትሕዊ በሆነ መንገድ እርዳታ እንዲያገኙ፣ በግጭት የወደሙ ንብረቶችን ለመተካትም እየተሠራ መሆኑም ተገልጿል። ትኩረት ከተሰጣቸው ጉዳዮች መካከል የተፈናቃዮችን ሰብዓዊ መብት ማስጠበቅ፣ ወደተፈናቀሉበት አካባቢ ከተመለሱ በኋላ መኖሪያ፣ ትምህርትና ህክምና እንዲያገኙ ማስቻል ተጠቅሷል።

ከተፈናቃዮች ጉዳይ ጋር በተያያዘ ተግዳሮት ከሆነው አንዱ ስለተፈናቃዮች የሚሰራጭ ሀሰተኛ መረጃ ነው ያሉት ቢልለኔ፤ “ለሰዎች መፈናቀል ምክንያት የሆኑ ግለሰቦች በሕግ ይጠየቃሉ” ብለዋል።

መፈናቀል፡ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የአንድ ዓመት ፈተናዎች አንዱ

እስካሁን በተለያዩ ክልሎች ግጭት በማስነሳት ከተጠረጠሩ 2517 ግለሰቦች መካከል 1300 ያህሉ በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ተጠርጣሪዎች በቅርቡ በቤንሻንጉል የተነሳውን ግጭት ጨምሮ በቡራዩ፣ በድሬዳዋና ሌሎችም አካባቢዎች ከተቀሰቀሱ ግጭቶች ጀርባ አሉ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መሆናቸውን ፕሬስ ሴክረተሪዋ ተናግረዋል።