May 10, 2019

ዘ-ሐበሻ

ክቡር ዶር ዐቢይ፦
ክቡር ዶር ለማ

የልባዊ ስጋት ሰላምታዬ ትድረስልኝ፡፡ ዛሬ ደካማ ሰውነቴን ከአገሪ ካወጣሁ ልክ 43 ዓመታት፦ከስድስት ወራት ኾኑ፡፡

በ66ዓም መጥቶብኝ የነበረው ስጋት ዓይነትም ተመለሰብኝ፡፡ በዚያን ጊዜ ን ነገሥቱን ፍጹም ሥልጣንን ለሕዝቡ በምክር ቤቱ አማካይነት እንዲመልሱ፦ ጠ።ሚኒስትሩ ም/ቤቱ ጠ።ሚኒስትሩን እንደመረጠ ሥልጣኑን እንዲያስረክብ፡ አዲሱ በሽግግርነት ሕገመንግሥቱ እንደጸደቀ አገር መሪውን/መሪዎቹን መርጦ እንዲያስረክብ ስል የነካካኋቸው ብዙሃን ባለሥልጣኖችን እንደነበሩ መረዳት አያስቸግርም፡~፡ በይበልጥ ደግሞ “ ሶሺያሎዝም_ ሶሺያሊዝም የሚሉትን ማስታወስ ይገባል፡፡

“ይህ ካልኾነ፦ የወገን ማለቂያ፦ የጠላት መሳለቂያ፦ የወገን መሳቀቂያ እንኾናለን!” ነበር መደምደምያዬ፡ ሳይኾን ቀርቶ እባሰ አዘቅትና ውርደት ውስጥ እንማቅቃለን፡፡

አኹን እድሜ ለእናንተ “ ተገላገልን!” ልንል ሲዳዳን እባሰ! አዎን “ እባሰ !” አደጋ ውስጥ ልንገባ ነው፡፡ ስለመለያያትና ላለመለያየት የኢትዮጵያ ሕዝብ የከፈለውን አባሪ ውስጥ ገልጫለሁ፡፡ ያኹኑ ግን ከመካከሉ፦ ከአ አ ከኾነ መለያየት ሳይኾን መደረማመስ ኾኖ “መበለጥ የማንፈልገው እኛ!” ሩዋንዳን እንደ ዋዛ እንድትታይ ልናደርጋት እንችላለን፡፡

1_ ክ ጠ ሚ ስለ”ዳያስፖራ” ጥቅም ማውራት ከንቱ ነው፡፡ አ አ እኮ ለባላገሩ  ልጆቹ ከአ አ በሚያድርጉለት እንደ “ ዳያስፖራ

አለማሰቡ ስህተት አይመለህም? ይህን ማስቀረቱስ አደገኝ አይሆንም፡፡ ስከዚህ በአስቸኳይ እንደደረሰህ

_ እስክንድር ነጋና የባልደራስ ጓደኞቹ ተገቢውና ሕጋዊው ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አውጀህ ትዕዛዝህን ማስከበር፦

_ መለስ ስዬን ለማሰር ባወጣው ሕግ ዓይነት ለአ አ የሾምኸውን የሚተካ ሕጋዊ ምርጫ በሦስት ወር እንደሚደረግ ማወጅና ማስፈጸም እስከነ ክብሩ ውጤቱ ያንተ ይኾናል፡፡   ካልኾነ ሥጋቱ .>

2_ ክር ዶር ለማ፦

ሀ_ በአ አ አካባቢ በሕገ ወጥነት ስለፈረሱት ቤቶች “ እኛው ያስቀመጥናቸው .።” ከማሻሻጥ እስከ ግንባታ ከዚያም መብራትና .   ግብር ለምክፈል ወዘተ “ናቸው!! ማለትህን የስማሁ መሰለኝ፡፡ ምንም ዓይነት ርምጃ ስለመወስዱ ግን . ..

_ ከንቲባ ተብዬዋ ቤ/ክ የተጠለሉትን እያየች “ እዚህ ምን ያደርጋሉ? አንድ ሰው ላይ አልፈልግም!” ስትል አልሰማህም፡?

እዚያው ላይ የ9 ዓመት ልጅ፦ ለምን ት/ቤት አትሄድም ሲባል የመልሰውንስ? “ ስመለስ ቤቴ ፈርሶ አገኘሁLል አኹን ደግሞ እናት አባቴን ላጣ ስለማልፈልግ.!።” የእኔስ ልጅ ቢኾን አያስብልም?

ምን አደረግህ? ርዳታ ስላለማግኘታቸው ማዕክላዊውን ( ፌደራል) ሃላፊ ሲጠየቅ “ ክልል ሳይጠይቀን ምንም ማድረግ አንችልም!” ካለ በኋላስ ምን ተደረገ?” እነዚህን እመሳሰሉ ግፍ አድራጊዎች ላይ ርምጃ  መውስዱና መገለጹ ለሕዝብ ድጋፍ አይጠቅምም?

*** ትልቁ ዳቦ ድግሞ ከሶማሌ ክልል ስለተፈናቀሉት ወገኖቻችን ወደነበሩብት ባስቸኳይ የመመለስ ርምጃ መጀመሩን መግለጽ ጥቅሙ ቀላል አይኾንም?  “  ለብልህ አይመክሩም.።!

አካሌ ውጪ መንፈሴ አገሬ ኾኖ ያላገናኘኋቸው በዚያች የጀግኖች አገር ላይ የሰይጣን ምልክትና አስማት እተለጠፈባት ባንዲራ እየተውለበባት ብገባ የጀኞቹን ክብር መድፈር ስለሚኾንብኝ፡፡ ስዚህም ነው ኤምባሴ ያልሄድኩትና የማልኬደው፡፡

ክቡራን ሆይ፦ ለእናንተ ባለኝ ክብር በአባሪነት የተዘጋጀውን ያላስተላለፍሁት እናንተው ከፈታችሁት፦ ለምን? ቁርሾ ለማብዛት!? ቢቻል ማጥፋት ነው፡፡ ደግሞም “የስብሰባችሁ ቀናትበመቃረባቸውኘው፡፡ ምክንያት አይጠበቅብኝም፡፡

ችግሮቻችሁ የሚገቡኝ ይመስለኛል፡፡

ቢኾንም የጉዳዩ አሳስቢነት እየጠጫነኝ እባካችሁ ኹለታችሁም ከኪዳነ ምሕረት (16//8፟) በፊት ጥያቄዎቼን አክብሩልኝ፡፤

አለበለዚይ በ17 እበትነዋለሁ፡፡

በመጨረሻ፦ ያው ያገር ጉዳይ ነውና፦ አቶ ስብሃት ነጋ “ሙስና ከመንግሥት የባሰ ቤ/ክ ውስጥ አለ፤፡” ማለቱ ያልሰማ የለም፡፡ ክቡርነትህም ሂሳቡ እንዲጣራ እንደምታደርግ ቃል ገብተህ ነብር፡፡ በዚያ በኩል ያለው ጉዳት ዘርፈ_ብዙ ነውና “ እባክህ!!!”

ዲያቆን ዳንኤል ቢፈልገኝ አይከፋም፡፡

አንድዬ አገራችንን ይጠብቅ ድካማችሁንም ለሰላምና ልፍሬ ያድርግልኝ

በተስፋ፤፟