May 11, 2019

አዲስ አባባ፣ ግንቦት 3፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ገዢው የአፍሪካ ብሄራዊ ኮንግረስ 57 ነጥብ 5 በመቶ ድምጽ በማግኘት አሸነፈ።

ገዢው ፖርቲ ሀገሪቱ ከአፓርታይድ አገዛዝ ነጻ ከወጣችበት ጊዜ ጀምሮ ለ25 ዓመታት ደቡብ አፍሪካን መርቷል።

የኤኤንሲ የአሁኑ ድል አፓርታይድ ከተወገደ በኃላ ለስድስት ተከታታይ የምርጫ ዘመናት በስልጣን ላይ እንዲቆይ ያስችለዋል ተብሏል።

ሆኖም የዘንድሮ ድሉ ከዚህ ቀደም ከተደረጉት የምርጫ ፉክክሮች ይልቅ ብዙ ድምጽ ያጣበት መሆኑ ተነግሯል።

ለዚህም በሀገሪቱ የተንሰራፋው ሙስናና ስራአጥነት በምክንያትነት ከተቀመጡ ዋነኛ ጉዳዮች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

የፓርቲው ምክትል ሴክሬታሪይ ጀነራልም በቀጣይም ከዚህ በፊት የሰራናቸውን ስህተቶች ማረም ይገባናል ብለዋል።

ባለፈው ዓመት ጃኮብ ዙማን የተኩት ስሪል ራማፖዛም ከሙስናና ከስራ አጥነት ጋር በተያዘ በቀጣዩ የመሪነት ዘመናቸው ፈተና እንደሚገጥማቸው ተንታኞች ገልጸዋል።

ምንጭ፦አልጀዚራ