
በአክሱም ኃውልት ላይ የተጋረጠው አደጋ ካልተፈታ ከዓለም ቅርስነት እስከመሰረዝ ያደርሰዋል ተባለ
በአክሱም ኃውልቶችና ተያያዥ ቅርሶች ላይ የተጋረጠው ችግር ባለበት ከቀጠለ ከዓለም ቅርስነት የመሰረዝ ዕጣ ሊገጥመው እንደሚችል የዘርፉ አጥኚዎች ተናገሩ፡፡ በአክሱም ኃውልቶችና ተያያዥ ቅርሶች ላይ ያጋጠመውን ስጋትና ቀጣይ መፍትሄ ለማመለካት ያለመ ሀገር አቀፍ አውደ ጥናት በአክሱም ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል፡፡
አደጋ በተጋረጠባቸው እነዚህ ቅርሶች ላይ ጥናት ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአርኪዮሎጂና ቅርስ አስተዳድር ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ሀጎስ በቀደምት አክሱማዊያን ተተክሎ እስካሁን እንደቆመ ያለው ቁጥር ሶስት ተብሎ የሚጠራዉ ኃውልት፣ ከጣሊያን ተመልሶ የመጣው ቁጥር ሁለት ኃውልት ሲተካል መናጋቱን ገልጸዋል፡፡
የተባባሪ አካላት አለመናበብና የህግና የማስፈጸም ክፍተት እንዲሁም ልማት በዘፈቀደ ማስፋፋት ችግሩ እየሰፋ እንዲሄድ እንዳደረገው ተባባሪ ፕሮፌሰር ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡
ችግሩ ባለበት ከቀጠለ የአክሱም ኃውልት ከዓለም ቅርስነት ሊሰረዝ ይችላልም ብለዋል፡፡ እ.ኤ.አ በ2010 አንድ የጣሊያን ኩባንያ ባቀረበዉ ጥናት መሰረት የተናጋውን ሀዉልት ለመጠገን 5 መቶ ሺህ ዩ ሮ ያስፈልግ የነበረ ሲሆን ፣አሁን ላይ ግን 3 ሚሊየን ዩሮ የሚጠጋ ሃብት እንደሚያስፈልግ በጥናቱ ተገልጿል፡፡
EBC