የሸገር የአርብ ወሬ
የኢትዮጵያ ልማት ምርምር ኢንስቲትዩት የሚባል ተቋም ከ20 አመት በፊት ተቋቁሞ ነበር፡፡ ተጠሪነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆኖ በሃገሪቱ የሚከናወኑ የልማት ክንውኖችን የሚያጠና እንዲሆን ነበር የተቋቋመው፡፡
በጀት ተመድቦለት ከሌሎች ሃገሮች በሚሰጥ የገንዘብ ድጋፍ ጓዳው የሞላ መሆኑ ቢነገርም ስለስራው ግን ብዙም የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ አሁን ደግሞ ከሌላ ተቋም ጋር እንዲዳበል ተደርጓል፡፡
ጥናት ሲያጠና ነው ቢባልም አሁን ያለውን ምጣኔ ሐብታዊ ድቀት አለማየቱ ወይም ይፋ አለማውጣቱ ጥያቄ ውስጥ ጥሎታል፡፡
Sheger FM102.1 ስለ ኢንስቲትዩቱ ጉዳይ የሚከተለውን አዘጋጅቷል፡፡