ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!
ታደሰ ቤጊ ማን ነው??

በሰፈሩ ልጆችና ጓዶቹ እንደተነገረው፤…
ታደሰ ቤጊ በአ.አ ከተማ በከ 18 ቀ 35 ከእናቱ ከወ/ሮ በቀለች ምትኩ ከአባቱ የሃ/አ ቤጊ ባልቻ በ 1942 መስቀል ፍላወር አካባቢ ተወለደ። ዕድሜውም ለትምህርት ሲደርስ እዛው ቀበሌ ጥበበ ገበያ 1ኛ ደረጃ ት/ቤ ገብቶ ካጠናቀቀ በኃላ ወደ ንፋስ ስልክ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ት/ቤ በመግባት የቮኬሽናል ትምህርቱን እስከ 10ኛ ክፍል ተምሮ ወደ አ.አ ተግባረ ዕድ ት/ቤት ተዘዋውሮ በአውቶ መካኒክ ፊልድ ተመርቋል።
ታደሠ በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ስለነበረ 12ኛ መልቀቂያ ፈተናውን በከፍተኛ ውጤት ስላጠናቀቀ ጀርመን አገር ትምህርቱን እንዲከታተል ዕድል በማግኘቱ ወደ እዛው ተጉዞ በመካኒካል ኢንጂነሪንግ ተመርቋል። ታደሠ በአውሮፓ እያለ ከብዙ ኢሕአፓ አባላት ጋር በቅርብ በትምህርት ቤት እየተገናኘ በአገራችን ፖለቲካ ጉዳይ ይመካከርና ይከራከር ስለነበረ፤ በጀርመን የኢሕአፓ አባል በመሆን በውጭ አገር የነቃ ተሳትፎ ነበረው። በኃላ ግን ወደ ውድ አገሩ ተመልሶ ጨፍጫፊ አረመኔውን ደርግ ለመፋለም ወሰነ። ገና የ27 ዓመት ወጣት እያለ 1967 ዓም ወደ አ.አ ተመልሶ ለተወሰነ ዓመት በአንድ መስሪያ ቤት ካገለገለ በኃላ፤ ደርግን በህቡዕ ተደራጅቶ በሚታገለው የኢሕአፓ ክንፍ ውስጥ ገብቶ ለዲሞክራሲ በቆራጥነት ታግሏል። ከዚያም በ 1969 መጨረሻ ላይ ብዙ አባሎች በአረመኒያዊው ደርግ እየታደኑ በ35 ቀበሌ ሜዳ በተለያየ ቀበናና በመሳሰሉት ቦታዎች እየታደኑ በጥይት ሲደበደቡ፤ በእርሱም ላይ የተጠናከረ ክትትል ስለነበር፤ ለጥቂት ቀናት ተደብቆ ከቆየ በኋላ፤ ከሌሎች ጓዶቹ (ሠመረ የሚባል በኋላ ደብዛው የጠፋ እና ያሲን የተባለ በአባቱ የመናዊ በእናቱ ኢትዮጵያዊ ውጣት) ጋር ከ አፓርታማ ሲወጣ ጠብቀው፤ ከተያዘ በኋላ ለእስር ተዳርጎ፤ አስከፊና አሰቃቂ ስዬል ተፈፅሞበት፤ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ፤ ከቤተስቡ መኖርያ ቤት ፊት ለፊት በመጣል፤ ሬሳውን ቀኑን ሙሉ አላፊ አግዳሚው እንዲመለከተው አድርገዋል። በዚያን ወቅት ይሄን ወንጀል ከፈፀሙት አንዱ የከ 18 ሊ/መ ካድሬ የነበረው “ንጉሡ ኡዚ ነው ትራሱ” ይባል ነበረ።
ታደሰ ቤጊ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!