May 12, 2018 ·

ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

እነኝህ ጀግ

Image may contain: 4 people

ና ወጣቶች እነማን ናቸው??

Image may contain: 4 people

የመጀመርያውን ጥይት የተኮሰው ኢሕአፓ ነው እያላችሁ ታሪክን የምታጨቀዩና የደርግን አረመኔነት ጥሩ ገፅታ ለመስጠት የምትሞክሩ ያለፈው ስርአት ወንጀለኞች እኛ በህይወት እስካለን ድረስ ማጋለጣችንና እውነቱን መናግርራችን ይቀጥላል!! እነኝህ ከታች የምታይዋቸው የ 14 አመቱን ባቢሌ ኅይለ ሥላሴ ጨምሮ ወረቀት በመበተንና በግድግዳ ላይ የደርግን ተቃውሞና ” ሕዝባዊ መንግስት ይቋቋም”፤ “ዲሞክራሲ ያለገደብ” ” ድርጅቴ ኢሕአፓ ነው!” ስላሉ ታስረው በግፍ የተገደሉ ናቸው። በዚያን ወቅት ኢሕአፓ አንድም ጥይት አልተኮሰም!!!!

የደርግ የግድያ ስምሪት በከፍተኛ 3ና በአካባቢው!!

የመጀመርያው ኢሕአፓን የማሳወቅ ሃገራዊ እንቅስቃሴ (mission) የተሳተፉትን ሕዳር 7 ቀን 1969 ዓም አራት ኪሎ ቤተመንግስት በደርግ ስብሰባ አዳራሽ ጠቅላላ ስብሰባ ተቀምጠው ሰው ለመግደል ተስማምተው ፀረ ሕዝብና ኢሕአፓ በማለት ከዚህ የሚከተሉትን የሕዝብ ልጆች ለደርግ ዘመቻና ጥበቃ መምሪያ ተእዛዝ ሰጥተው አዲስ አበባ ውስጥ ባልታወቀ ቦታ ጀግኖቻችንን ረሽነው ጥለዋል።

መኮንን ወዳጆ
ዳንሄል ኃይሌ
ውብሸት ሰይፉ
ተስፋዬ ሁንዴ
ንጋቱ ተሰማ
አሉላ ደበሳይ
ክፍሉ የማነ ብርሃን
ይስሐቅ ቢተውልኝ
አበበ ዋቄ
ደጀኔ ሰብስቤ
ጫን ያለው ካሣ
ደጀኔ በርሔ
ኢዮብ ገለሴ
ተሾመ አሰፋ
ታደለ እጅጉ
ኃይሌ ወልዴ ራህመቶ
ምትኩ ረመቹ
ተስፋ ማርያም ተስፋ ጋብር
ተስፋዬ ዳኜ
ክንፈ ዋቄ
ጌጡ አበኔ
አዳነ በቀለ
ለማ አበበ
ባቢሌ ኃይለ ሥላሴ
ተከስተ ወልደ ስላሴ
ግርማ ሰለሞን
ግርማ ቶሎሣ

አንድነት ሃይል ነው!!!
ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO) ይቀጥላል!!!