Ethio-Online

May 12,2019  3:33 PM ·

2019-05-13 Author: ጌጥዬ ያለው

ሠራተኛው የህብረተሰብ ክፍል የእተጨቆነ መሆኑ ተገለፀ

42ኛው አመት በአለም ሰራተኞች በዓል እለት የተሰው ሰማዕታት መታሰቢያ ዝግጅት በአዲስ አበባ፤ የቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም ተከብሮ ውሏል።

በዝግጅቱ ላይ ታሪካዊ ዳሰሳ ያቀረቡት ደራሲ፣ጋዜጠኛ እና የቀድሞው ፖለቲከኛ ክፍሉ ታደሰ አሁንም ሠራተኞች ችግር ላይ መሆናቸውን ገልፀወል። እንደ እሳቸው አባባል ከደርግ ዘመነ መንግስት ጀምሮ እየተነሱ ያሉ የሠራተኞች መብቶች እስካሁን አልተመለሱም።

ገዥውን ፓርቲ ጨምሮ የፖለቲካ ድርጅቶችም የሰራተኛውን ጥቅም ማዕከል ያደረገ እንቅስቃሴ እያደረጉ አይደለም ተብሏል።

በበዓሉ ዝግጅት ላይ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ቢጋበዙም አልተገኙም። ወደ ሃያ ለሚደርሱ የመንግሥት ተቋማት ጥሪ ቢደረግም አንዳቸውም አልተገኙም።

ደራሲ፣ጋዜጠኛ እና የቀድሞው ፖለቲከኛ ክፍሉ ታደሰ በ42ኛው አመት የሜይ ዴይ ሰማዕታት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ፤ ከቀይ ሽብር ሰማዕታት መታሰቢያ ሙዚየም ከቀረበው የቀጥታ ስርጭት የቀጠለ፤

https://www.facebook.com/ethionline7/videos/445907409493780/