እኔ ኦሮሞ ነኝ። ሚንሊክ ጡትም፣ ብልትም አልቆረጠም እላለሁ። ታሪክ እናውራ ካልን ብልት መቁረጥ በኦሮሞ ባህል ይበዛ ነበር። ዘር እንዳይራባ ከተፈለገም ጡት አይቆረጥም፤ የወንድ ብልት እንጂ። ሚንሊክ አባት እሆንሃለሁ፣ ልጅ ሁነኝ በማለት ነው የዘመቱት።
ለመወቃቀስም፣ ለመሸላለምም ካስፈለገ ከሚኒሊክ ብቻ መጀመር የለብንም። አፄ ሚንሊክ ስልጣን የያዙበትና አፄ ዮሐንስ የሞቱበት በአንድ አመት ውስጥ ነው። አፄ ዮሐንስ በእስልምና ተከታዮችና በአማራ ላይ የሰራው ግፍ ግን በዚህ 50 አመት አንድም ጊዜ በክፉ ተነስቶ አያውቅም። የችግራችን መነሻም ይሄው ነው።

