May 15, 2019
Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 7፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በነገው ዕለት ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) በነገው ዕለት በሚያካሂደው ስብሰባ በብሄራዊ ደህንነትና ሌሎች ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያል፡፡
ኮሚቴው ለውይይት በሚቀርብ ሰነድ ከተወያየ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል ተብሎ እንደሚጠበቅ የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽህፈት ቤት አስታውቋል፡፡
ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በቅርቡ ባካሄደው ስብሰባ በአጭር ጊዜዎች ውስጥ በተከታታይ እየተገናኘ ስራዎችን በጋራ እንዲገመግምና አቅጣጫዎችን እንዲያስቀምጥ መግባባት ላይ እንደደረሰ ጽህፈት ቤቱ አስታውሷል፡፡