May 16, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/117290

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በብሄራዊ ደህንነት ጉዳዮች ላይ በመወያየት ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ
(ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ግንቦት 8 ቀን 2011 ዓም ባካሄደው ስብሰባ ባለፈው አንድ ዓመት የለውጥ ጉዞ ውስጥ የተከናወኑ የብሔራዊ ደህነንት ስኬታማ ስራዎችን እንዲሁም እያጋጠሙ ያሉትን ተግዳሮቶች የገመገመ ሲሆን የመፍትሄ አቅጣጫዎችንም አስቀምጧል።
ኮሚቴው የሀገሪቱን ብሔራዊ ደህንነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎችን በጥልቀት የተመለከተ ሲሆን ለአብነትም በውጭ ሀገራት የነበሩ የታጠቁ ኃይሎች ትጥቃቸውን ፈትተው ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መደረጉ እንዲሁም ከኤርትራ ጋር የነበረው ሰላምም ጦርነትም ያልሆነ ግንኙነት መስተካከሉ ከለውጡ በኋላ የተገኙ ስኬቶች መሆናቸውን ገምግሟል፡፡ከለውጡ ማግስት ጀምሮ በጸጥታና ደህንነት ተቋማት የሪፎርም ስራዎች መካሄድ መጀመራቸው፤ የደህንነት ተቋም አመራሮች ከፖለቲካ ወገንተኝነት የጸዱ እንዲሆኑ የሚያስችል የአመራር ለውጥ መደረጉን በጠንካራ ጎን የገመገመው የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የመከላከያ ሰራዊት ባለፈው አንድ ዓመት ጠንካራ ሪፎርም ካደረጉ ግንባር ቀደም ተቋማት አንዱ እንደሆነና ከአደረጃጀቱ ጀምሮ አጠቃላይ የመከላከያ መዋቅሩን ለማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች መከናወናቸውንም አይቷል፡፡
ባለፈው አንድ ዓመት በአጠቃላይ በጸጥታው ዘርፍ ጠንካራ ስራዎች ቢከናወኑም በርካታ ተግዳሮቶች እያጋጠሙ መሆናቸው ኮሚቴው ገምግሟል፡፡
ተግዳሮቶቹ በዋናነት ከጽንፈኛ ብሔርተኝነት፣ ከኢ-መደበኛ አደረጃጀቶች ወይም ደቦዎች፤ ከህገ-ወጥ የጦር መሳርያ ዝውውር እንዲሁም ከማህበራዊ ሚድያ ሀሰተኛ ዜናዎች ተጽዕኖ ጋር የተያያዙ መሆናቸውንም ተመልክቷል፡፡
እነዚህ ተግዳሮቶች ለዜጎች ሞት፣ መፈናቀልና የደህነንት ስጋት ምክንያት መሆናቸውንም አስምሮበታል፡፡
ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው በብሔራዊ ደህንነት ጉዳይ በጥልቀት ከተወያየ በኃላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡
በዚህም ብሔራዊ ደህንነ