May 23, 2019

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ብርሃን ሰላማዊ ሠልፍ ተካሄደ፡፡ ሰላማዊ ሠልፉ መፈናቀልና ግድያን በማውገዝ ነው እየተካሄደ ያለው:: ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንዲቆምም ሠልፈኞቹ ጠይቀዋል::

Image may contain: 1 person, standing, crowd, sky and outdoor

የአማራ ወጣቶች ማኅበር በሸዋና የሸዋ ተወላጅ አማራዎች በጥምረት ያዘጋጁት ሠልፍ በደብረ ብርሃን እየተካሄደ ነው::

ሰላማዊ ሠልፉ መፈናቀልና ግድያን በማውገዝ ነው እየተካሄደ ያለው:: ማንነትን መሠረት ያደረገ ጥቃት እንዲቆምም ሠልፈኞቹ ጠይቀዋል::

ፍትሐዊ የሀብት ክፍፍል እንዲኖርና የደራ አማራ አስመላሽ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱም ጠይቀዋል:: በየቦታው ለሚፈጠር የአማራ መፈናቀልና ግድያ የፌደራል መንግሥት ምላሽ እንዲሰጥ ጠይቀዋል:: እስካሁን የደረሰውንም ጥፋት አውግዘዋል::

የክልሉ መንግሥትም ለችግሮቹ መፍትሔ በአጭር ጊዜ እንዲያስቀምጥ ጠይቀዋል:: ሠላማዊ ሠልፉ አስፈላጊ መልዕክቶን አስተላልፎ በሠላም ተጠናቅቋል፡፡

Image may contain: 2 people, people walking, crowd, shoes, hat, tree and outdoor
Image may contain: 1 person, standing, shoes, sky, crowd, tree and outdoor