
እስር እና ወከባ ትግልን አያቆምም – የመቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ
ከረጅም ውጣ ውረድ በሗላ የኢትዮጵያ ህዝብም የአማራ ህዝብም እኩልነት እና ነጻነት መጣ ብሎ ተስፋ ሲያደርግ ተረኛ ነኝ በሚል ኦህዴድ ከግንባር ፓርቲው ህወሃት የተማረውን የዘረኝነት አካሄድ ማስቀጠል የፈለገ በመሆኑ እና ምልክቶችንም በማየቴ የአማራ ህዝብ ለተጨማሪ ባርነት እንዳይዳረግ ወጣቱን እና ፋኖውን እያደራጀን እንገኛለን።
፨ ከትናንት የእስር ትእዛዝ በፊት ደብረ ዘይት ላይ የማፈን ሙከራ ተደርጓል።ይህንን ከክልል እስከ ፌደራል ያሉ የአዴፓ ባለስልጣኖች ያውቃሉ።እኔ የሄድኩበት መኪና በመንግስት አፋኞች ክትትል ውስጥ ስለገባ በአየር ሃይል መኪና አዲስ አበባ ገብቼ ለማምለጥ ችያለሁ።
፦ የfb አካውንቴ ለአራት ጊዜ ዘግተውታል።
፦ ከሀገር እንድወጣ ምክር በዶ/ር አምባቸው ተሰጥቶኛል።
፨ዶ/ር አምባቸው ወደ ክልል እንዲመጡ በአዲስ አበባ እና ባህርዳር ከፍተኛ ጥረት አድርጌያለሁ።ነገር ግን ጥሪ ተደርጎልኝ ወደ ቢሯቸው ስሄድ ከሀገር ወጥቼ የተወሰነ እረፍት አድርጌ እንድመለስ የመከሩኝ ሲሆን የወጣት አደረጃጀቱ መዋቅራዊ ቅርጽ ሳይዝ እና ገና በሁሉም አካባቢ ሳይመሰረት የትም ሀገር የመሄድ ፍላጎት እንደሌለኝ አሳውቄ ነበር።ንግግራቸው ሲተረጎም “ውጣልኝ “ነው እንጂ ለእኔ አስበው አይደለም።በነገራችን ላይ አሁን እኔ እየሰራሁት ያለው ስራ ራሱ የክልሉ መንግስት መስራት የነበረበት እና ለእነሱም ድጋፍ እንጂ ስጋት ነው ብዬ አላምንም።

፨የሰማእቱ የሳሙኤል አወቀ ጉዳይ የተጣራ መረጃ ስለነበረኝ አሁን የደረሰበትን እና ስጋቴን ገልጨላቸው እንደሚረዱኝ ቃል ገብተዋል።ነገር ግን አጣሪ ኮሚቴው አጣርቶ መያዝ ያለበት አካል እንዳለ አሳውቀው ፖሊስ ኮሚሽን ከአንድ ወር በላይ ሁኖታል ምንም ነገር የለም።
እኔ ደግሞ ለህዝብ ቃል ስለገባሁ የደረሰበትን ደረጃ በእየጊዜው አሳውቃለሁ።
ለጊዜው በሁለት ሰዎች ላይ የእስር ትእዛዝ ቢወጣም እስካሁን አልተያዙም ተጨማሪ ምርመራምጠለጊዜው ቁመሟል። ምክንያቱ አይታወቅም
፨ከትናንት በፊት ግንቦት 13/14 ሌሊት በስልክ ከእኛ ተቆርቋሪዎች ባ/ዳርን ለቀን እንድንወጣ ትእዛዝ ተሰጠን።ምክንያቱ ደግሞ የእስር ትእዛዝ በእኔ እና በዘመነ ካሴ እንደወጣብን እና የፌደራል መንግስት በሚስጢር ይዞ ሰው እንደላከ ሰማን።ነገር ግን ፖሊስ እፈልግሃለሁ በተባለ ቁጥር ከቤት ወጥቶ መጥፋት አስፈላጊ ባለመሆኑ እና ማስለመድም ስሌለለብን ከቤታችን ሁነን የሚመጣውን ሃይል አቅም በፈቀደ እራሳችንን ለመከላከል ወስነን ተቀመጥን።
፨በዚህ ጉዳይ ከሶስት የአዴፓ ስራ አስፈጻሚዎች ውጪ ማንም አያውቅም።
፨ይህንን የምጽፈው አዴፓ ስህተት ነው የሚል መረጃ ማውጣቱን በመስማቴ ነው።ሲጀመር መግለጫ ማውጣት ያለበት የክልሉ መንግስት ወይስ አዴፓ?

፨አሁንም የእስር ትእዛዙ መቅረት አለመቅረቱን አላውቅም።
በዚህ አጋጣሚ የባህርዳር ወጣቶች፣ፋኖ እና ህዝቡን ከልቤ ለማመስገን እፈልጋለሁ።
በአሁኑ ወቅትም ወጣቱ እና ፋኖው የእኔን ቤት ዙሪያውን እየጠበቀ ይገኛል።
፨እዚህ ላይ መናገር የምፈልገው በአማራ ክልል በሁሉም ቦታዎች የምትገኙ ወጣቶች እና ፋኖዎች በተረጋጋ መንፈስ መንቀሳቀስ እና ለፌደራል የጸጥታ አካል ምክንያት እንዳንፈጥር ማስተዋል አለብን።የእስር ትእዛዙን ተከትሎ ጥሩ ያልሆነ ነገር ቢፈጠር እንኳን ወደእርስ በእርስ እልቂት እንዳናመራ እና የጠላት መሳቂያ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን።

፨ከዚህ እውነታ ውጪ በአካባቢ፣ በጎጥ እና በዝምድና ብዙ ዋጋ የከፈሉ አክቲቪስቶቻችንን እና ወጣቶችን ለመከፋፈል እና ትልቁ የአማራ ህዝብ ትግል እንዲዳከም የክልሉ መንግስትም ሆኑ የአዴፓ አመራሮች የምታደርጉትን እንቅስቃሴ እንድታቆሙ ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
ለሁሉም የአማራ አክቲቪስቶች
፨የአማራ ህዝብ ትግል የነጻነት እና የእኩልነት እንጂ ተደግፎ እና ተደጉሞ የማይድነውን አዴፓን ሰውን በሰው ለመተካት አይደለም።
፦ ኦዴፓ ከ2000 በላይ አመራሮችን ሲቀይር አዴፓ ምን አደረገ?
————————————————————————
1/ የወጣቶችን የስራ እድል ፈጠራ ቀንሷል?
2/ የሃይስኩልን እና የዩኒቨርሲቲ ምሁራንን አጋር በማድረግ አስጠግቶ እያማከረ ነው?
3/ ከላይ ያሉ አንድ እና ሁለት ሰዎች ቦታ ከመቀያዬር ውጪ በየዞኑ እና ወረዳው ህዝቡን ሲያሳፍኑ እና ሲያስገድሉ የነበሩ ሰዎች አሁንም በቦታቸው አይደለም ያሉት?
4/ከክልሉ ዉጪ ለሚኖረው አማራ ተወካይ በመሆን በትንሹ የመኖር መብታቼው እንኳን ተከብሮላቸዋል?
በየዩኒቨርሲቲው ያለሉ አማራዎች ተረጋግተው እንዲማሩ እየተደረገ ነው?
# ሁሉንም ጥያቄዎች መልሶ ከሆነ መቀየር ያለበት ሰው ሊሆን ይችላል።
፨በእኔ እይታ ግን ለውጥ የሚባል ነገር የለም።ስለዚህ መቀየር ያለበት ህገ መንግስቱ፣የፌደራል ስርአቱ እና ኢህአዴግ እና አዴፓ ነው።
፨እነዚህ ከላይ ያሉት እስካሉ ድረስ ዶ/ር አምባቸው ተነስተው አቶ ዮሀንስ ቢሆኑ ለውጥ ሊያመጡ አይችሉም።ነገር ግን ስርአቱ ሲወድቅ የአማራን ህዝብ እንዳያጠፋ በአንድ ላይ ቁመን ተቋም መገንባት ጸጥታችንን ማስከበር እና ማደራጀት አለብን።
፨ስለዚህ በማህበራዊ ሚዲያ ከዚያም ከዚህም በምታገኙት ያልተሟላ መረጃ ትችት ላይ እንዳትወድቁ መጠንቀቅ አለባችሁ የሚል ምክር አለኝ።
፨የራሳችንን ሰው ቢያጠፋ እንኳን ደግፈን ጸሃይ እንዳይመታው ማድረግ እንጂ ሞራሉን የሚነካ ጽሁፍ በመለጠፍ ታጋዮቻችንን እንዳታርቁብን ስል አሁንም ጥሪዬን አስተላልፋለሁ።
ትግላችን ይቀጥላል!