======================================
ስዩም ተሾመ ከመስከረም አበራ ጋር ያደረገውን ቃለምልልስ ተጀምሮ እስኪያልቅ አዳመጥሁ አቶ ስዩም ለአለው አዲስ አስተዳደር ደጋፊ እንደመሆኑ መልካም የሚባል ፍልሚያ አድርጓል። የዋዛ ያልሆነችው ትንታጓ ምሁር፣ አንደበተ እርትዑ ለሁሉም ፈታኝ ጥያቄወቹ ከእርሱ በተለየ እይታ (Paradigm) መልሱን በአስገራሚ ሰጥታዋለች።

እኔን እየገረመኝ የመጣው ግን የሴት ታጋይ ምሁራን የመንፈስ ጽናት ትናንት በዚያ ትውልድ ያየሁት ዛሬ ሲደገም ማየቴ ነው። እድሜ ደጉ ይባላል። እውነት ነው እንደመስከረም አበራ፣ እርዮት አለሙ እና ገና ያልወጡ ጽኑ የሀቅ ታጋይ እና ምሁር ሴት ዜጎችን ማየት ምን ያህል እንደሚያኮራ መግለጽ ይሳነኛል። የመስከረምን መልስ እና አመለካከት ጥልቀት እና ምስጢር ለመዘርዘርም ሆነ ለመተቸት አቅም ይጎድላል እላለሁ። ለሁሉም ዝርዝር ቆየት ብየ ስለምመልስበት ለግዜው ግን ስሜቴን ለመግለጽ ያህል ይህችን ብያለሁ። ግን ሁሉም እንዲያዳምጠው በትህትና እጋብዛለሁ።