ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ካሳሁን ወርቁ ሹምዬና እነዚህ 39 ላብ አደሮች እነማን ናቸው??

በሰለሞን ክፍሌ (ጌሌ)እንደተነገረው፤…..…

ካሳሁን ወርቁ ሹምዬ ከአባቱ ከሻምበል ባሻ ወርቁ ሹምዬ እና ከእናቱ ወ/ ጥሩነሽ በሐረር ክ/ሀገር ከድሬዳዋ ወጣ ብላ በምትገኝ ኤረር ጎታ ተብላ በምተጠራ ትንሽ ከታማ ተወለደ። የ 1ኛ ደረጃ ትምህርቱን አዲጋላ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ከተማረ በኋላ፤ ወደ ድሬደዋ ተዘዋውሮ ከ 9ኝ እስከ 10 በ ልኡል መኮንን 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትሏል። ከዚያም እስከ 12ኛ ሐረር መድሃኒአለም ት/ቤት ተምሮ፤ አዋሽ ሸለቆ ይገኝ በነበረው የአሚባራ እርሻ ልማት ውስጥ ተቀጥሮ ሲሰራ፤ ሠራተኛውን አደራጅታችኋል፤ ሠራተኛውን ለስራ ማቆም አሳድማችኋል በማለት፤ በሰላማዊ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ከነበሩትና በግፍ በጅምላ ከተገደሉት 40 የላብአደሮች፤ የሠራተኛ መሃበር መሪዎች አንዱ ነበር።

የደርግ ፋሺስትነት ገጦ እየወጣ መምጣት ሲጀምርና፤ ገና ኢሕአፓ በሰላማዊ ትግል እየተንቀሳቀሰ በነበረበት ወቅት (ሚያዝያ/1968)፤ አገር አንቀጥቅጡንና በመላው ኢትዮጵያ ሠራተኞች አንድነት ማሃበር (ኢ.ሠ.አ.ማ) በተጠራው የስራ ማቆም አድማ ተሳትፋችኋል በመባል 40 ሰላማዊ ኢትዮጵያውያኖች በግፍ ሲገደሉ ከኢሕአፓ በኩል አንድም ጥይት አልተተኮሰም ነበር። ኢሕአፓ እራሱን ለመከላከል አንድም ጥይት መተኮስ ሳይጀምር፤ አረመኔው ደርግ ይሄን የመሳሰሉትን ትርጉም የለሽና የህዝብ ቅስም የሚሰብር ወንጀሎችን ፈፅሟል።

በዚያን ወቅት ሻምበል ባሻ ጌታቸው ሺበሺ ( በኋላ ጄነራል የሆነው) በመባል ይታወቅ የነበረውና፤ ባረመኔነቱ ተወዳዳሪ የማይገኝለት፤ እጁ በንፁሃን ደም የተጨማለቀ ወንጀለኛ የመንግስቱ ሃይለማርያም ቀኝ እጅና የደርግ አባል፤ እነኝህን 40 ለመብታቸው በሰላማዊ መንገድ ሲታገሉ የነበሩ ላብ አደሮች ከሚሰሩበት አዋሽ ሸለቆ ይዞ በአዋሽ እስር ቤት ካሰራቸው በኋላ፤ አሰበተፈሪ ወደሚገኘው እስር ቤት ተዘዋውረው፤ በጅምላ ተረሽነው በጅምላ ተቀብረዋል።

ይሄ ከዚህ በታች ያለው ልብ የሚሰብር ግጥም ለነዚህ ንፁሃን ኢትዮጵያውያኖች በኢሕአፓ ልሳን ላይ የተገጠመ ነው፤…

አንቺ አዋሽ በርሃ
መስክሪ ምድሪቱ
ለኒያ ላብ አደሮች ለተረሸኑቱ

ጩሂ አስበተፈሪ
እሪ በይ በቅጡ
እኒያ ላብ አደሮች
ከየት እንደመጡ

የደምም ደም አለው
የነጎድጓድ ጩኽት
ብራቅ ነው ይፋጃል
የላባደሩ ሞት
የነጻነት እሳት!!!!

ካሳሁን ወርቁ ሹምዬና እነዚህ ላብ አደሮች በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ናቸው። በጣም እንኮራባቸዋለን!!!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!

Image may contain: ‎text that says '‎"トめやrの λતની aeද みかใい "-のל‎'‎