May 24, 2019

«ብሔርን ማዕከል ያደረገ ፌዴራሊዝም ለኢትዮጵያ ስለማይበጅ ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ የሚያመጣ ፌዴራሊዝምን እንተገብራለን» – የኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ
(ኢ.ፕ.ድ)

ሰሞኑን በአገሪቷ እየተናፈሱ ካሉት ወሬዎች መካከል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ፓርቲ መመስረት አንደኛው ነው። ከዚህ በፊት የተለያዩ ፓርቲዎች እንዳቋቋሟቸው ህብረት፣ ቅንጅት፣ አማራጭ ኃይሎች፣ መድረክን እንደመሳሰሉት ፓርቲዎች ሁሉ ይህም እንደነሱ ይዳከማል ይፈርሳል፤ የሚሉ ግምቶች በአንድ በኩል ሲኖሩ በተቃራኒው አሁን ካለው ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ኢዜማ የተሻለ ሊሆን ይችላል የሚሉም አልታጡም።

በኢትዮጵያ የፓርቲዎች ታሪክ ውስጥ ከተለያዩ ፓርቲዎች ተቀናጅተው የሚመሰረቱ ፓርቲዎች ከኢህአዴግ ውጪ አንድ ፓርቲ ሆነው በመዝለቅ መንግሥት ሲመሰርቱ አልታየም። ይልቅ የመፈረካከስ እና የመሰንጠቅ አደጋ ሲያጋጥማቸው ተስተው ሏል።

ኢዜማ ግን እንዲህ እንደማይሆን እና መንግሥት እስከመሆን ሊዘልቅ እንደሚችል የተናገሩት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ ናቸው። ይህንን እና ሌሎች ጥያቄዎችን አክለን ከኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ ጋር ቃለምልልስ ያካሄድን ሲሆን፤ ከኢዜማ ምክትል ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ ጋር የነበረንን ቆይታ እንዲህ አቅርበንላችኋል።

ሙሉ ቃለምልልሱን ለማንበብ ሊንኩን ይጫኑ https://www.press.et/Ama/?p=11334#
► መረጃ ፎረም – JOIN US