May 29, 2019

ተጋሩ በአማራ ክልልና በመላው ኢትዮጵያ፣ አማራዎች በቤኑሻንጉልና በመላ ኢትዮጵያ፣ ኦሮሞዎች በሶማሌና በመላ ኢትዮጵያ፣ ጌደኦዎች በኦሮምያና በመላው ኢትዮጵያ፣ ሶማሌዎች በዓፋርና በመላ ኢትዮጵያ ወዘተ በብሄራቸው ምክንያት ጥቃት ሳይደርስባቸው እንደ ዜጋ በእኩልነት የሚኖሩበት ስርዓት በመገንባት የሀገራችን አንድነትና የህዝባችን ደህንነት እንጠብቅ!

አብሮነትንና አንድነትን እንስበክ! ስለብሄርና ስለመለያየት የምናወራ ከሆነ ግን መጠቃቃቱ የሚቀጥል ይሆናል። የትግራይ ብሄር ተወላጅ የሆነው ተማሪ የተገደለው በብሄሩ ምክንያት ከሆነ፣ የአማራ ተወላጆች በጉሙዝ የተገደሉት በብሄራቸው ምክንያት ከሆነ በብሄር መገዳደሉ የብሄር ፖለቲካ ውጤት ነው።

የብሄር ፖለቲካ ውጤቱ መጠቃቃት ከሆነ ለምንድነው የሚያስፈልገው? ለመገዳደል? የብሄር ፖለቲካ ካልቆመ በብሄራቸው ምክንያት የሚጠቁ ዜጎች ይበዛሉ! ሰው ግን በብሄሩ ሳይሆን በምግባሩ ሊዳኝ ይገባል። ሰው በብሄሩ ምክንያት ሲጠቃ መስማት ያማል። ዜጎች በማንነታቸው ሳይሸማቀቁ በፈለጉት የኢትዮጵያ አከባቢ ተዘዋዉረው የመስራትና የመኖር ዕድል ሊያገኙ ይገባል። በብሄር ማሰብ ካላቆምን ማንነት መሠረት ያደረገ ጥቃት ይቀጥላል! መቆም አለበት!”