May 29, 2019
Source: https://mereja.com/amharic/v2/120799
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/A7D14F0D_2_dwdownload.mp3
የአሐዱ ራዲዮ ጣቢያ ኃላፊን ጨምሮ የጣቢያዉ አራት ባልደረቦች ሰንዳፋ ፖሊስ ጣቢያ ቃላቸዉን ሰጥተዉ ፍርድ ቤት ለመቅረብ በዋስ መለቀቃቸዉን አስታወቁ።የጣቢያዉ ኃላፊ ጋዜጠኛ ጥበቡ በለጠ እንደሚለዉ እራሱን ጨምሮ አራቱ ጋዜጠኞች ለመጪዉ ሳምንት ሐሙስ ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ቀጠሮ ተስጥቷቸዋል።አንድ የአሐዱ ራዲዮ ጣቢያ ጋዜጠኛና ሌላ ባልደረባዉ «የተዛባ ዘገባ» አሰራጭታችኋል በሚል ፖሊስ ባለፈዉ አርብ አስሮ ሰኞ ነበር የፈታቸዉ።ጋዜጠኛ ጥበቡ እንደሚለዉ የፖሊስ ርምጃ የጋዜጠኞችን የመዘገብ ነፃነት የሚጋፋ ነዉ። DW
Audio Player00:000
