May 29, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/120783

የዓለም ባንክ 350 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ለኢትዮጵያ አጸደቀ:: ከዚህ ውስጥ 70 ሚሊዮኑ እርዳታ ሲሆን 280 ሚሊዮኑ አነስተኛ ወለድ የሚከፈልበት የረጅም ግዜ ብድር ነው::

ገንዘቡም የአርብቶ አደሩን ህይወት በሚያሻሽሉ ተግባራት ላይ ይውላል:: ከዚህም በተጨማሪ ባንኩ 200 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ዋስትና ለኢትዮጵያ ያጸደቀ ሲሆን: ይህም በመንግስትና በግል በጋራ ለሚለሙ የኤሌክትሪክ ኃይል ኢንቨስትመንት ዋስትና የሚሰጥ ይሆናል::

ዋስትናው እስከ 1.5 ቢሊዮን የአሜሪካን ዶላር የግል ኢንቨስትመንት እንደሚስብም ይጠበቃል:: ገንዘቡ ለኢትዮጵያ ብድርም ሆነ እርዳታ አይደለም:: ዋስትና ነው::

ይህም ማለት ኢንቨስተሮች ሶቨርን ወይም የመንግስት ዋስትና ሳይጠይቁ ኢንቨስት እንዲያደርጉ ስለሚያደርግ የኤሌክትሪክ ኃይል ኢንቨስትመንትን በጣም ያበረታታል:: ዋስትናው የሚመለከታቸው 6 ፕሮጀክቶች ለአብነት ተያይዘዋል::
Via Fistum Arega