
ኦነግ ከአሁን በኋላ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ሰራዊት እንደማይኖረው ከዕርቀ ሰላም ኮሚቴው ጋር በሰጠው መግለጫ አስታወቀ።
በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እና የእርቀ ሰላም ኮሚቴው በጋራ ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
የዕርቀ ሰላም ኮሚቴውና የሃገር ሽማግሌዎች በሃገር ውስጥ ሲንቀሳቀስ የነበረውን የኦነግ ታጣቂ ሰራዊት ወደ ካምፕ ለማስገባት የተከናወኑትን ተግባራት የመጨረሻ ሪፖርታቸውንም አቅርበዋል፡፡
በጋራ በሰጡት መግለጫም ኦነግ ከአሁን በኋላ ታጥቆ የሚንቀሳቀስ ሰራዊት እንደማይኖረው አረጋግጧል።
የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ በበኩላቸው የመንግስት ጥሪን ሰምተው ለተመለሱ የሰራዊቱ አባላት መደበኛ ህይወታቸውን እንዲመሩ መንግስታቸው ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸል፤ ለቀጣዩም ለሰላማዊ ትግልም መንግስት በሩ ምንጊዜም ክፍት መሆኑን አረጋግጠዋል። — ENA