May 29, 2019
Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ኤርትራ አሜሪካ በፀረ ሽብር ዘመቻ በትብብር አብራቸው ከማትሰራባቸው ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ሰረዘች፡፡
በዛሬው ዕለት በአሜሪካ የፌዴራል መዝገብ ይፋ ይሆናል ተብሎ በሚጠበቀው ውሳኔ ኤርትራ በሽበር ጉዳዮች ከአሜሪካ ጋር በትብብር ከማይሰሩ ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ትወጣለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
አስካሁን ድረስ ኢራን፣ ሰሜን ኮሪያ፣ ሶሪያ እና ቬኒዙዌላ ሽብርን በመከላከል ከአሜሪካ ጋር በትብብር ከማይሰሩ ሀገራት መካከል ይገኛሉ፡፡
የአሜሪካ ድምፅ የእንግሊዘኛ ክፍል ኤርትራ ባለፈው ዓመት ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ሰላም ስምምነት እስከተመለሰችበት ጊዜ ድረስ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የተገለለች ሀገር ነበረች ብሏል በዘገባው፡፡
እንዲሁም ኤርትራ ባለፈው ከኢትዮጵያ ጋር ወደ ሰላም መመለሷን ተከትሎ በተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ተጥሎባት የነበረው ማዕቀብ እንደተነሳላት የሚታወስ ነው፡፡
የአሜሪካ ኮንገረንስ አባላት ከ14 ዓመታት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በተያዘው የፈረንጆች ዓመት መጀመሪያ ላይ በኤርትራ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።
ምንጭ፡- ቪኦኤ