ኢሕአፓዎች ፤ ቁጥር ሁለት፤ 21/05/2019
የግለኝነት፣ የስግብግብነት፣የሙሰኝነት ወዘተ..ፀሮች
የጎሰኝነት፣የጎጠኝነት ፣ የጠባብነት፣የትምክህተኝነት ወዘተ..ጠላቶች
የእኩልነት ፣የሕባዊነት፣ የአንድነት ወዘተ..ተምሳሌቶች
የሥነ ስርዓት (ዲሲፕሊን) እና የዓላማ ጽናት ምሳሌዎች
[የሰባአዊነት ፣የትኅትነት፣የሰው አክባሪነት፣የታዛዥነት፣
የሕዝብ ልጅነት ወዘተ..በተባር ገላጮች
የሰፊው ሕዝብ ህመም ፣ብሶትና እከክ ዳሳሾች
[የሰፊው ሕዝብ መራብ፣ መታረዝና መጎሳቁል አልቃሾች
[በየበረንዳው ፣በየጎዳው ፣በየድልድዮች ሥር ፣በየጉራንጉሩ ወዘተ.. ተዳዳሪዮች፤
መከራና ፍዳ] አዛኞች ፣ እንባቸውን ተካፋዮች
መንግሥት፣ ወገን እንዲደርስላቸው አቤት ባዮች ፤ ጯህዮች
አሁንኑ መፍትሄ ይፈለግ ባዮች
ኢ ሕ አ ፓዎች – [የጭቁን አርሶ አደር ፣የጭቁን ወታድር ፣የጭቁን ላብ አደር የጭቁን ሴት ፣የብሄር ብሄረሰቦች ] ፍጹም አጋሮች ነበሩ፤ ናቸው።
– ለብሄር ብሄረሰብዎች [ባህል፣ ቋንቋ፣ ልማድ ወዘተ..]
– እኩልነት ይከበር!
– ለዳር ድንበር ጠባቂው ጭቁን ወታደር የደሞዝ እድገትና ኑሮ ይሻሻል!
– በዝቅተኛ ገቢ ለሚኖሩ ሠራተኞች ደሞዝ ይጨመር ፣ ሕይወት ይሻሻል!
– ለአፈር ገፊው ጢሰኛ የመሬት ባለቤትነት መብት
– ይኖረው !
– የፆታ መድሎ ይቁም ! ሴቶች እንደ ሁለተኛ ዜጋ መቆጠር የለባቸውም ! ከወድሞቻቸው ጋር እኩል ዜጋ
ናቸው !
– የሃገራችን ሃብት የጥቂት ባለሥልጣኖች መንደላቀቂያ መሆን የለበትም !
– የሃገራችን ሃብት በትክክል ለሰፊው ሕዝብ ይዳረስ ወዘተ.. በማለት ፤ተጋድሎዋል ፣ የሕይወት ዋጋ ከፍለዋል
ታጠቅ
ኢሕ አፓዎች ፤ ቁጥር አንድ
Sat, May 18, 2019 9:58 pm
ኢሕ አፓዎች ፤ ቁጥር አንድ
ኢ ሕ አፓዎች ፦ የሰፊው ሕዝብ ልጅዎች
[ለፖለቲካዊ ፣ ለሰባዊ ፣ለሃይማኖታዊ ወዘተ ..
መብቶች] ተጋዳዮች
ለሕግ የበላይነትና ለማኅበራዊ ፍትኅ] ጠበቆች
ዲሞክራሲያዊ ሕዝባዊ መንግሥት አሁንኑ ባዮች
[የመጻፍ ፣ የንግግር ፣ የመሰብሰብ ፣ የመወያየት –
(ለአደባባይ ሕይወት) መብቶች ተሟጋቾች፤ሟቾች
ኢሕ አ ፓ ዎች፦ በሀገራችን የመጀመርያ የፖለቲካ ፓርቲ ምሥራቾች
ስለመደብለ የፖለቲካ ምንነት አሥተማሪዮች
[በአገራችን የመደብለ/የብዝሃን የፖለቲካ ፓርቲ ሥርዓት
አሥፈላጊነት አስተምሮት] አንጋፋዎች
ኢሕ አ ፓ ዎች ፦ [ለግዜያዊ ጥቅም ፣ ለአጭር አቋራጭ ሥልጣን
በአገሬና በህዝቤ ጥቅም ላይ አልደራድርም] ባዮች
የፖለቲካ ሽርሙጥናና አጎብዳጅነት አክ-እትፍ ባዮች
[ለሀገራቸው ሉዓላዊነት ፣ ዳር ድንበራቸውን ላለማስደፈር ፣
የሕዝባቸውን ጥቅምና ክብር ] ሕይወት ገባሪዮች
[ በየደረሱበት ፣ በየዋሉበት ፣ በየረገጡበት – አገሬ ፣ ሕዝቤ ፣
ታሪኬ ፣ባህሌ ፣ ቋንቋዬ ወዘተ.. ] ባዮች ፣ ተቆርቋሪዮች
ታጠቅ ዙርጋ
