========================
የዴሞክራሲ መርህ አንዱ የዜጎችን ባሻቸው መደራጀትን መቀበል፣ የተሰማቸውን በተቃርኖ ሲያሰሙ መብት መሆኑን ማወቅ ማዳመጥ የዜጋ ቅሬታን ለውይይት ማብቃት፡፡

በዚህ አንጻር አንዳንድ ለዴሞክራሲ ታግልን ያሉ ግለሰቦች በአደባባይ መንግስት ያለውን ብቻ ደግፉ ሲሉን ምን እንበል?

በብርሀን ፍጥነት ከተቃዋሚነት ወደ የመንግስት ካድሬነት ሲለወጡም አየን፡፡
የዘር ፖለቲካ በተንሰራፋባት ኢትዮጵያ የፖለቲካውን ፈጣሪወች ደግፈው ሌላውን ዘረኛ ሲሉም ታዘብን

ትግሉ በጎመራበት ወቅት ከየጎሬው ተደብቀው በባታልየን አደራጀን፣ አስታጠቅ፣ መድፍና ታንክ አዘጋጀን ብለውም ቀሰቀሱን፡፡
ሁሉንም አደረጉልን፣ ዜጋም አፍ የለው አይናገር፣ ተሸብቦ እና ሰሚ ጠፍቶ ታጋይም፣ አደርጃም፣ የመንግስት አፍ እና ጀሮም ነን ሲሉ ሞራል ስለሚባለው ይሉንታ ብንጠይቅስ ይፈረድብናል?

እስክንድር ነጋን ስለመብት መጠየቁን እንደጭራቅ ሲስሉት እና የዘር አባወራወችን ዛሬም እንደትናንቱ ተሸክመው ተቀበሉን ሲሉ የአቋማቸው ምንነትን ብንጠይቅ ያስወቅሰናል?

ከቅርብ ግዜ ወዲህ ተቃዋሚ ነን፣ በኢትዮጵያ የተንሰራፋውን ወያኔአዊ ስራት እንታገላለን ብለው አብረውን ሰልፍ የወጡ ተገልብጠው የአዴፓ እና የኦዴፓ ባለስልጣናት ወደውጭ ሲወጡ የድርጅቶች አባላትን በሚያስንቅ አራጊ ፈጣሪ ሲሆኑ ስናይም የሞራል እና የመርህ ዳር ድንበሩ የት ነው ብለን ብንጠይቅ ሊያስወቅሰን ይገባል?

A single lifetime is enough if it is lived with principles.
Malika Nura