ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!
መምህር በሪሁን ገ/ህይዎት ፤ መምህር አስረስ ካሳ ፤ መምህር ዋርዬ አዲ ፤ መምህር ካሱ መኮንን ፤ መምህር ተከስተ ገ/መስቀል ፤ መምህር ፀጋዬ መኮንን እነማን ናቸው ???

ቅድመ 1966 የነበረው የ አፄው ስርአት የፈጠረው የፍትህ ፤ ዲሞክራሲና እኩልነት መዛባት ህዝባዊ አመፅ ሲፈጥርና ሲቀጣጠል የተለያዩት የህብረተ ሰብ ክፍሎች ድርሻቸውን ሲያበረክቱ የአስተማሪዎችም ሚና ከፊተኛ እንደነበር ታሪክ አሳይቶናል። በኢትዮጵያ የትግል ታሪክ ውስጥ መምህራን በመምህራን ማህበር ስር ብሎም በኢህአፓ ስር በህቡዕ በመደራጀት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክተዋል የህ ነው የማይባል መስዋእትነት ከፍለዋል።
የሌላው የህብረተ ሰብ ክፍል የራሱን ፍትሃዊ ጥያቄዎችና ዲሞችራሲ ጥያቄዎች አንግቦ ሲነሳ አስተማሪዎችም የራሳቸውንና አገራዊ ጥያቄዎች አንግበው ለፍትህና ዴሞችራሲ ታግለዋል ተዋድቀዋል። ሴክተር ሪቪውን በመቃዎም የተነሳው የአስተማሪዎች እንቅስቃሴ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍሎች ፤ ከሰራተኛው ማህበር ፤ ከታክሲ አሽከርካሪዎች ፤ ከዩኒቨርሲቲ አስተማሪዎች ፤ ከተማሪዎች፤ ከለሎችም በመተባበር 4 ቀን ከቆየውና 85,000 አባላትን ላካካተተው ሰራተኞች ማሃበር መሬት አንቀጥቅጥ የስራ ማቆም አድማ የማያወላዳ ድጋፍ ሆነው ስርአቱ መውደቅ እንዳለበት አስመስክረዋል።
ከላይ የተጠቀሱት 6 መምህራን በኢህአፓ ስር ታቅፈው ከፋሺስት ደርግ ጋር በትግል የተዋደቁና የተሰዉ እንቁ የኢትዮፕያ ጀግኖች ናቸው!! አሁንም ከወያኔ ጋር እየተዋደቁ ላሉት ወጣት አስተማሪዎች አርአያ ናቸው!!!
ፋሺስቱ ደርግና ወያኔ በኢትዮፕያ ምድር ላይ የመጡ የጥፋት መልእክተኞች እንደሆኑ ማሳየታችን ይቀጥላል!!!!!! ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ ነውና ሁለት አራጆችን ስናወዳድር ጊዜአችንን አናባክን!!! ወዳጅና ጠላት ለይተን አንድነት እንፍጠር!!! ብለንም ከፊታችን አግጦ ያለውን ቫንፓየር ወያኔ ባንድነት እናስወግድ!!
በፋሺስቶችና በዘረኞች የተሰውትን ሰማእታት መዘከራችን የማያቆም ነው። ይቀጥላል!!!!!!!!!!!!!!!!
በደቡብ ኢትዮጵያ ደርግ ያካሄደው ግድያና ሽብር መቸም የሚረሳ አይደለም ። ሻለቃ አሊ ሙሳና ጌታቸው ሺበሺ፤ ካድሬዎች እነ ሟቹ አሰፋ ጫቦ፤ መቶ አለቃ ጴጥሮስ ገብሬ ወዘተ ብዙ ለጋ ሕይወት አጥፍተዋል ። ግፉን ወያኔም ቀጥሎበታል ።
መቶ አለቃ ጴጥሮስ ገብሬ የአውራጃው አስተዳዳሪ በነበረበት ወቅት ከሌሎች በተለይም ኑሩ አበጋዝ ከሚባል ከአዲስ አበባ ከተላከ ካድሬ ጋር በመተባበር አያሌ ታጋዮችን አሰቃይተው ገድለዋል ። በ1971 ዓ.ም እነዚህ አረመኔዎች ኢሕአፓ ብለው ከገደሏቸው ፤ በጥይት ደብድበው አንድ ጉድጓድ ውስጥ ከቀበሯቸው ውስጥ የሚከተሉትን ስም ለዝክር እናቀርባለን ። ሁሉም የተገደሉት በአጀር ሲሆን ቀኑም ሰኔ 25/1971 ዓ.ም. ነበር ።
• ማቴዎስ ጡምሮ፤
• ነጋ ዘለቀ
• ወ/ር ዮሴፍ ገበየሁ
• አሥራት ዓለሙ
• አበባው በጸሓይ
• ወ/ር ስንታየሁ መኮንን
• ወ/ር በረከት ዮሴፍ
• ፋንታሁን መዘምር
• ጥላሁን ጊንዶሎ
• ዮሓንስ ኤርጌቶ
• ወ/ር መኮንን ዘውዴ
በነሓሴ 21/1971 ዓ.ም. ደግሞ በጨጨ ኢሕአፓ ተብለው በጥይት ተደብድበውው በነ መቶ አለቃ ጴጥሮስና በሊሎች በአንድ ጉድጓድ የተጣሉት የህዝብ ልጆች የሚከተለት ናቸው።
• አድማሱ ዘውዴ
• አስናቀ ካሳ
• አድማሱ ወንድሙ
• አድማሱ ከስሜ
• አያህልኝ ቢረዳ
• አባይነህ ንጉሴ
• ደመቀ ቦጋለ
• ተሾመ ነጋሽ
• አምዴ አድማሱ
• ፍቅሬ ለገሰ
• ታደሰ ተሾመ
• ካሱ እምሩ
• ሉሉ ደምሴ
• አዳነ ገብሬ
• አባተ ረታ
• አሰፋ በቀለ (ሃኪም)
• አክሊሉ ፈለቀ
• መኮንን አዳነ
• ሞገስ ግርማ
• ወ/ር ጸጋዬ ኃይለማርያም
•
ከላይ ይተዘረዘሩትን የሕዝብ ልጆች መቶ አለቃ ጴጥሮስና ግብረ አበሮቹ በጠቋሚዎች በመጠቀም ወደ ሆሳዕና መጥተው እንዲታስሩ ያደረጓቸው ናቸው ። በተለይ አስታጥቄ ፈለቀ የሚባል አንጃ ብዙዎቹ ላይ ጠቋሚ በመሆን አስከፊ ሚና ነበረው። ሁሉም የተገደሉት አሰቃቂ ግብረ ስየል ከተፈጸመባቸው በኋላ ነው ።
ጸረ ሕዝቡና ዘረኛው የወያኔ ቡድንም ሥልጣን በጠመንጃ ሃይልና በባዕዳን ድጋፍ ከያዘ በኋላ ምርጫ እያለ ሕዝብን ለማደናገር ቧልቱን ሲያካሂድ በሀዲያና ከምባታ፤አለባ ትምባሮ ዞኖች በ1992-93 (በአውሮፓውያን አቆጣጠር 2000-2003) በተደረጉት የተውካዮችና የክልል ምክር ቤቶች ምርጫ ወቅት የማይደግፉትን የህዝብ ልጆች በጠራራ ፀሃይ አሊያም በውድቅት በራቸውን እየሰበረ አፍሶ ገድሏቸዋል ። ብዙዎችንም ለአስከፊ ስደት ዳርጎ ከዚህም አትርፎበታል
ወያኔ የገደላቸው የህዝብ ልጆችም ስም ዝርዝር እነሆ፤
በሃዲያ ሰሮ ወረዳ በኩማንኤቶ ቀበሌ በ 27/2/1992 በጥይት ተደብድበው የተገደሉ–
• አቶ ደመቀ ሆማጎ
• አቶ ዘለቀ ኤርጌቶ
በ29/7/92ና በ 30/6/92 በዋለጋበታ
• ጌጩጮ አርጥበ
• ተማሪ ኤርጃቦ ዋኖሬ
በሶሮ ወረዳ በአምሾረ ቀበሌ በ 6/9/92 በሚበሉበት ቤት በቦምብ የተገደሉ ባልና ሚስት ( በወያኔ ምርጫ ማጭበርበር አንካፈልም ስላሉ)
• አቶ ሚሻም ካቢሶ
• ወ/ሮ አልማዝ አንሰቦ
( ህጻን ሴት ልጃቸውን ትተው የተሰዉ)
በዚሁ ጊዜ ደግሞ በሌሞ ወረዳ በጂሮ ቀበሌ
• ወ/ሮ ባርዲቱ ሺፋና
• ወ/ሮ ማዝዲያ ሸኩራላ በጥይት በወያኔ ተገድለዋል ።
በባድዋቾ ወረዳ በዌራ ማዘሪያ ቀበሌ ደግም በ26/8/93 በወያኔ ወታደሮች የሚከተሉት የህዝብ ልጆች ተረሽነዋል–
• አቶ ዓለሙ ቡንጤሶ
• አቶ ሀማቾ ሁንቤቦ
• አቶ ደምሴ ብልጤቦ
• አቶ አብርሃም ከበደ
በከምባታ ጥም
በከምባታ ጥምባሮ በፍርዘኖ ቀበሌ በ 27/6/93 ከተገደሉት የህዝብ ልጆችና ወገኖች ውስጥ የሚከተሉትን ስም እንጠቅሳለን፤
• ዘለቀ በየነ
• አብርሃም ፋንጋ
• ወ/ሮ አዳነች አሞሬ
በሉዛምብራ ቀበሌ ደግሞ አቶ ዳንኤል በየነ፤ አቶ ለማኮ ቦቤቶ፤አቶ ደና ማሎሬን የምንረሳቸው አይደሉም ። በዱርጊ ቀበሌ ካልንም አቶ ደነቀ ደሳለኝ፤ አቶ መኮንን መስቀሉ የሚዘከሩ ናቸው ። አቶ ኤርሚያስ አብዩን ከቃጭቢራ ቀበሌም የምንረሳቸው አይደለም ።
ደርግም ወያኔም ሕዝብ ፈጅተዋል፤ሽብርም አካሂደዋል ። ዛሬ ለኢትዮጵያ ሲከፈል የቆየውን መስዋዕትነት ልንረሳ ልንዘንጋ የወገን ደም አይፈቅድልንም ። ነፍሰ ገዳዮችን ታጋይና ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ አድርገው ሊያቀርቡ የሚጥሩትንም መቃወም ግዴታችን ነው ። ብዙ ደም ፈሷል ። ዜጎች ለሀገራቸው ሲሉ ተሰውተዋል–ውድ ህይወታቸውን ሰጥተዋል ። የምናከብራቸው ጠላቶቻቸንና ገዳዮቻቸውን በማቀፍ ሳይሆን በማጋለጥና በማውገዝ ብቻ ነው ።
የህዝባዊ ፍርድ ቀን መምጣቱ አይቀርም !!
ይሄንን አረመኔ ፋሺስት ደርግ ነው ያሁኖቹ የድል አጥቢያ አርበኞችና የወያኔ አጋፋሪዎች አገርወዳድ የሚሉን!!
እነኝህ ያለፉ ጓዶቻችን በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ናቸው። በጣም እንኮራባቸዋለን።
የጠፉ፤ ያለፉ፤ ህይወታቸውን ለትግሉ የሰጡ ኢንዲሁም የተሰዉ ጓዶቻችንን የማስታወስ ብሎም የቆሙለትን አላማ ግብ የማድረስ ሃላፊነት ኢትዮጵያዊ ግዴታችን ነው!!!!
ወያኔ፤ ወያኔነትን፤ ጽንፈኝነትን፤ጎጠኝነትን፤ በአንድነት እንዋጋ!! አንድነት ሃይል ነው !!!
ኢትዮፕያዊነት ምንግዜም አቸናፊ ነው!!!!!
ነፍስ ይማር ለጀግኖቻችን!!!
የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!
