June 2, 2019

ኢሳት እንዲጠፋ ለምን ተፈለገ ለሃሳብ ነጻነት እንታገላለን ለሚዲያ ብዣነት እንተጋለን የሚሉ ሰዎች ሳይቀሩ ኢሳት እንደ ትርፍ አንጀት ተቆርጦ እንዲወድቅ አይን ያወጣ ዘመቻ ከጀመሩ ሰነባብተዋል። የራሱ ሰዎች ከሚባሉ ፖለቲከኞች ጀምሮ እስከ ጎሰኞች ድረስ ኢሳትን ሲገዘግዙት እያየን ነው።

እርግጥ ነው። ኢሳት ጥፋቶች እና አጥፊዎችን ታቅፏል። ሆኖም ግን ጥፋቶችንና አጥፊዎችን የማረም የመፍትሔ ስራ መሰራት ሲገባው ኢሳትን በጥብጦ ታማኝ ተቃዋሚ ለማድረግና ከእውነት የሚያፈነግጥ ሚዲያ ለማድረግ የተሴረው የፖለቲከኞች ሴራ ግማሽ መንገድ አልፎ ሔዷል።

ይህ አካሄድ አደገኛ ከመሆኑም በላይ ኢሳትን አስከሬን አድርጎ ወደ ቀብር ስፍራ መውሰድ ስለሆነ ግብዓተ መሬቱ ከመፈጸሙ በፊት ኢሳት ላይ ነብስ ዘርቶ ሕዝባዊ የሚዲያ ተቋም ማድረግ ያስፈልጋል። እውነት ትቀጥን ይሆናል እንጅ አትበጠስም። ሁሉም ወገን ተመካክሮ፡ሰክኖና ተወያይቶ ኢሳት ይበልጥ ጠንክሮ እንዲወጣ እንደምትሰሩ እምነት ያለን ሰዎች አለን፡፡ጎራ ለይቶ መጠዛጠዝ ለማንም አይጠቅምም፡፡

በሳልነት የሚታይበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ይህ በሳልነት ኢሳትን ከሚያንኮታኩቱት ፖለቲከኞችና ሴረኞች ማዳን ነው። ኢሳትን ወደ ሕዝብ ሚዲያነት መልሶ ከኢሕአዴግ ጥገኝነት ለማላቀቅ ሁሉ እንደቀድሞው ድርሻውን ሊወጣ ይገባል።ኢሳትን የኢሕአዴግ ጥገኛ ማድረግ ያሳፍራል። ፖለቲከኞች ብቻ ሳይሆኑ ሻእቢያም በአቅሙ ኢሳትን ለማፈራረስ የሴራ ሚና ከሚጫወቱት አንዱ ነው። ሕወሐትም በተዘዋዋሪ እጁን መስደዱን እየሰማን ነው።ይህ የሕዝብ ሚዲያን ለመቅበር የአዞ እምባ እያነቡ የሚያጅቡት ሁሉ ለኢሳት ችግር ተጠያቂ ናቸው።#MinilikSalsawi