ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ጂሃድ አባ ዲኮ ማን ነው??

Image may contain: 1 person

በ አብይ ተፈራ እንደተነገረው፤.

ጂሃድ አባ ዲኮ ከአባቱ አባ ዲኮ ማናና ከእናቱ .…በጂማ ከተማ ተወለደ። እድሜው ለትምህርት እንደደረሰ ጂማ በሚገኘው የ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን ሚያዝያ 27 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እስከ 12ኛ ክፍል ከተከታተለ በኋላ ደርግ ያዘጋጀው “እድገት በህብረት የእውቀትና የስራ ዘመቻ” ላይ ዘምቷል። ጂሃድ አባ ዲኮ በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ከሚባሉት ውስጥ የሚመደብ ሲሆን የታወቀ የቅርጫት ኳስ ተጫዋችም ነበር።

ጂሃድ አባ ዲኮ ከዘመቻ መልስ በኢሕአፓ ስር ተደራጅቶ ለሕዝባዊ መንግስትና ለዴሞክራሲ መብቶች ሲታገል፤ ደመቀ ሃረገወይን የተባለ ቅጥር ነፍሰ ገዳይና የህዝብ ድርጅት ሃላፊ ገድለሃል በመባል ተይዞ፤ በጂማ ፖሊስ መምርያ ለከፍተኛ ስዬል ተዳርጎ፤ ስድስት ወር በወህኒ ከታሰረ በኋላ፤ ከሌላ 34 ወጣቶች ጋር አብሮ፤ በ 1970 ዓ.ም በጥር ወር በደርግ ቅጥር ነፍሰ ገዳዮች በግፍ የተገደለ ድንቅ ወጣት ነበር።

ከጂሃድ አባ ዲኮ ጋርና በተለያየ ጊዜ ከተገደሉት ወጣቶች በጥቂቶቹ፤…..
(በዚያን ወቅት ጂማ ውስጥ በነበሩ ወጣቶች ወይም ቤተ ዘመዶች የያንዳንዱን ሰማእታት አጭር ታሪክ እንደደረሰኝ ፅፌ ለንባብ አቀርባለሁ)

ሰኢድ ያሲን
ተስፋዬ በፍቃዱ
ዘሪሁን አሉላ
አስራት ዱላ
ታደለ ጂዳ
ገዛኽኝ እሸቱ
ገዛኽኝ ገዳ
ፋሲል ሙሉጌታ
ሰኢድ አሊ(ባሬ)
አሙቲ አባዋሪ

ሁሴን አባዋሪ
ክበበ ገ/ፃድቅ
ሚዛን
ትግስት ክፍሌ
መሃመድ ሰኢድ አባ ሰሞር
አማረ ገሰሰ
ሁሴን አባዋሪ
አንዋር አህመድ
ዝናብ አባጨብሳ
በደዊ ሀቢብ
ጌቱ አስማማው
በቀለ ተፈራ
(አቡዋንጃ) ከድር
ፀጋዬ ቆጭ
ሚሊዮን ቆጭ

ጂሃድ አባ ዲኮ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!