Source: https://mereja.com/amharic/v2/122156

የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ግብረ ሰዶማውያን ታሪካዊ ቦታዎችን እንዳይጎበኙ ጥሪ አቀረበ
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ኢ- ግብረ ገባዊ የሆኑት ግብረ ሰዶማውያን የሀገር ቅርስና ታሪካዊ ቦታዎችን ኢላማ ያደረገ የእንገናኝ መልእዕክቶችን መንግስት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ጥሪ አቀረበ::
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጠቅላይ ፀሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጥም በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠይቀዋል።
ጠቅላይ ፀሃፊ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ግብረ ሰዶማዊነት ከኢትዮጵያ ሃይማኖቶች ፣ባህልና ህግ ጋር የሚፃረር በመሆኑ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ እንደሚያወግዘውም ተናግረዋል።
