ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

ታደለ ጂዳ ማን ነው??

Image may contain: 1 person

በ አብይ ተፈራ እንደተነገረው፤.

ታደለ ጂዳ ከናቱ ከ ወ/ሮ ዘለቃ ገ/ማርያምና ከአባቱ ሻምበል ጂዳ.. በጂማ ከተማ ተወለደ። የ 1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን እዛው ጂማ ውስጥ ይገኝ በነበረው ሚያዝያ 27 1ኛና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ገብቶ ተከታትሏል። ታደለ ጂዳ በትምህርቱ በጣም ጎበዝ ከመሆኑም በላይ በጣም ተጫዋች፤ ትንሽ ትልቁን አክባሪና በህዝብ የተወደደ ድንቅ ወጣት ነበር።

ታደለ ጂዳ በወቅቱ በነበረው የደርግ “እድገት በህብረት ዘመቻ” ለተወሰነ ጊዜ የተሳተፈ ሲሆን፤ ከዛም መልስ በከፍተኛ ደረጃ በኢሕአፓ ውስጥ በመሳተፍና ወጣቱን በማደራጀት ግዴታውን የተወጣ ጀግና ወጣት ነበር። በኋላም በደርግ ነፍሰ ገዳዮች እጅ ወድቆ አስከፊ ግ/ስዬል ተቀብሎ፤ ምንም ፍንክች ሳይል፤ የድርጅቱን ሚስጥር እንደጠበቀ ለስድስት ወራት ያህል በጂማ ወህኒ ቤት ከታሰረ በኋላ፤ ከሌላው ጀግና ከጂሃድ አባ ዲኮና ሌሎች 34 ወጣቶች ጋር በግፍ ተገድሏል።

ታደለ ጂዳ በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!


የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!