ሁሌ እናስታውሳቸው
ተቀብሮ እንዳይቀር
አኩሪ ታሪካቸው!!!!!!!

አብርሃም ገብረኪዳን ማን ነው??

Image may contain: 1 person, closeup

አብርሃም ገብረኪዳን በ አዲስ አበባ ከተማ በ 1950 ዓ.ም ተወለደ። 1ኛ ደረጃ ትምህርቱን ካጠናቀቀ በኋላ 2ኛ ደረጃ ትምህርቱን በኮልፌ አጠቃላይ ት/ቤትና በተፈረ መኮንን ት/ቤት ገብቶ ተከታትሏል። አብርሃም በወቅቱ በነበረው የተማሪ እንቅስቃሴ ውስጥ በጣም ጉልህ ሚና የነበረው የነቃ ወጣት ነበር።

ኢሕአፓም ከተመሰረተ በኋላ በኢሕአፓ ወጣት ክንፍ (ኢሕአወሊ) ስር በመደራጀት በወቅቱ ከነበረው የፋሺስቱ መንግስቱ ሀ/ማርያም አምባገነን መንግስት ጋር በቆራጥነት ሲታገል ከቆየ በኋላ በ 1970 ዓ.ም በህዳር ወር በደርግ ነፍሰ ገዳዮች በግፍ ተገድሎ በመርካቶ ውስጥ ከአመዴ ገበያ ፊት ለፊት ቀይ ሽብር ተብሎ ተጥሏል። አብርሃም ገብረኪዳን በዚያን ወቅት የ 20 አመት ወጣት ነበር።

አብርሃም ገብረኪዳን በአሁኑ ሰአት ከወያኔ ጋር እየተዋደቀ ላለው ወጣት ትውልድ አርአያና ምሳሌ ነው። በጣም እንኮራበታለን!!!!!

የተለያዩ የህዝብ ልጆችና ሰማዕታት አጭር ታሪክ (BIO)ይቀጥላል !!!