June 5, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/122325

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በአክሱም ዩኒቨርሲቲ አንድ ተማሪ እንደሞተ ጠቁሞ የሚከተለውን የሀዘን መግለጫ አውጥቷል

የሀዘን መግለጫ!

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ዛሬ 27/09/2011 ዓ/ም በኣክሱም ከተማ ለሞተው ኣንድ የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ ተማሪ የተሰማው ጥልቅ ሀዘን በትግራይ ህዝብና መንግስት ስም ይገልጻል፡፡

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በተማሪው ላይ የተፈፀመው ኣስነዋሪ ድርጊት ኣጥብቆው እንደሚኮንነው እና ግድያው የፈፀሙትን ግለሰቦች ለህግ ለማቅረብ እተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ኣስፈላጊው ሁሉ እንደሚያድርግ ያስታውቃል ፡፡

በመጨረሻም ለሞች ተማሪ ቤተሰቦች ፣ዘመድ ወዳጅች የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት መፅናናት ይመኛል፡፡

የትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የህዝብ ግንኙት ቢሮ
መቐለ፡ ግንቦት 27/09/2011 ዓ/ም