June 5, 2019

Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ፣ግንቦት 28፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ)ዶክተር ንጉሴ ምትኩ የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው ተሾሙ፡፡

ዶክተር ንጉሴ የህዝብ ተወካች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ ነው በዋና ስራ አስፈፃሚነት የተሾሙት፡፡

የቀድሞው የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ስዩም መኮንን በገዛ ፈቃዳቸው ሃላፊነታቸውን መልቀቃቸውን ተከትሎ ነው ሹመቱ የተካሄደው፡፡

ሹመቱ በምክር ቤቱ አባላት አስተያየት ተሰጥቶበት በአራት ድምፀ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ ፀድቋል፡፡

በሶዶ ለማ