♣መንግስታችን በግብረሶዶሞች ጉብኝት ላይ ግልጽ አቋሙን ሊያሳውቅ ይገባል!!♣
ባለፉት ዓመታት ስለግብረሶዶም መስፋፋት ለነኦባማን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጫና ቦታ ሳይሰጡ በቆራጥነት አቋማቸውን አሳውቀው ምድራቸው እንዳይረግጥ ያደረጉና ህዝባቸውን የጠበቁ ግንባር ቀደም መሪዎች፦

♥የዝምባቡዬው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ ቀዳሚ ሲሆኑ ከ30 ዓመትታ በፊት በሃራሬ በተዘጋጀው 50ኛው የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጉባኤ/WCC/ አንድም የግረ ሰዶም አራማጅ ቤተ እምነትም ሆነ ግለሰብ ወደ ሃገሬ መግባት አይችልም። በሃገሬ ውስጥ ይህን የሚያራምድ ካለም በአደባባይ ላይ ይሰቀላል። በማለት ቆምጨጭ ያለ አቋማቸውን ገልጸው ነበር።
♣በመቀጠል የታላቋ ሩስያ መሪ ቪላድሚር ፑቲን ሲሆኑ ከአራት ዓመት በፊት በሞስኮብ ተዘጋጅቶ በነበረው የክረምት ፓራ ኦሎምፒክ ስፖርት ለአንድም ግብረሰዶማዊ በተሳታፊ ሃገሮች የሚገኙ ኢምባሲዎች ቪዛ ካርድ እንዳይሰጡ ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፈው ነበር።በዚህም አሜሪካንን ተበሳጭታ ብዙ ተሳታፊዎቿ ቀርተዋል።
♦Uganda’s leader has signed into law a bill toughening penalties for gay people.
It includes life sentences for gay sex and same-sex marriage.
US President Barack Obama had cautioned the bill would be a “backward stage”.
“Homosexuality is just bad behaviour that should not be allowed in our society” MP David Bahati
Lesbians are covered by the bill for the first time.
The bill originally proposed the death penalty for some homosexual acts.
ግብረሶዶማዊያን ወደ ሃገራችን በመንግስት እውቅና ተሰጥቶት የገባው ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም የጤና ሚኒስቴር በነበሩበት ጊዜ በሃገራችን በተዘጋጀና የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ትንሹ ቡሽ በተሳተፈበት የዓለም አቀፍ የጤና ጉባኤ ነው።
በዚህ ግዜ ሶዶማውያኑ ለግዜው ስሙን መጥራት በማይገብልኝ ካሳንችስ በሚገኝ ሆቴል የራሳቸውን ጉባኤ ሊያደርጉ እንዳቀዱ ተወርቶ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ግን በተባበሩት መንግስታት ECA የስብሰባ አዳራሽ አድርገዋል።
ይህ እንዳይደረግ በወቅቱ የነበረው የሃይማኖቶች ጉባኤ አስቸኳይ ስብሰባ አድርጎ ውይይት በማድረግ ጠንከር ያለ የተቃውሞ የአቋም መግለጫ ተዘጋጅቶ የነበረ ቢሆንም የሃይማኖት መሪዎቹ እዛው ሳይበተኑ ዶ/ር ቴዎድሮስ በደህንነቶች ታጅቦ ፈጥኖ በመድረስ “ሃገራችንን እርዳታ ያሳጣታል ከአሜሪካ ጋር ያጣላናል” በሚል ዛቻና ማስፈራራት ተጽእኖ መግለጫው ሳይተላለፍ እንደቀረ አስታውሳለሁ።
በሰ/ት/ቤት ወጣቶችና ማህበራት የተቃውሞ ሰልፍ እንዳይወጣ በደህንነት አካላት ከፍተኛ ወከባ ሲደረግ እንዳመሸ አስታውሳለሁ።
ዛሬስ አሁን በሃገራችንም ሆነ በአሜሪካ ያሉ መሪዎች ከአለፉት እምነትየለሽ መሪዎች በተለዬ ለየሃገራቸው እምነትና ባህል ታሪክ ልዩ ትኩረት የሚሰጡ ሲሆን በተለይ ፕሬዚዳንት ትራምፕ ወደ ስልጣን እንደመጡ ኦባማ ሊወርዶ 3 ወር ሲቀራቸው የፈረሙትን ግብረሰዶምን በመላው አሜሪካ ህጋዊ የሚያደርግ ሰነድ በመቅደድ በአሜሪካ ምድር ግብረሰዶም ቦታ የላቸውም በሚል ኢ-ህጋዊነታቸውን በህግ አስቀምጠው ለዓለም ህዝብ በቴሌቪዥን ፊርማቸውን አሳይተዋል።
በሃገራችን አዲሱ ለውጥ ያመጣቸው ጠ/ሚኒስትራችንም ላለፉት 45 ዓመታት ከነበሩት የኮምኒዝም አቀንቃኝ ፀረ – ሃይማኖት መሪዎች በተለዬ መልኩ ለሃይማኖት ተቋማት በሃገራችን ሊኖራቸው ስለሚገባቸው ሚናና በየተቋማቱ የነበሩ ልዩነትምችን አቀራርበው በማስታረቅና ወደ አንድ እንዲመጡ በማድረግ፤ በሲኖዶስ ስብሰባና በረመዳን ኢፍጣር ተገኝተው ሰፊ ንግግር አድርገዋል።
♥በመሆኑም መንግስት ለሃገሪቱ ህዝቦች እምነትና ባህል ለማክበር ይህን ያህል ከተጓዘ፤ ይህን ታሪክ እምነትና ባህል የሚያቆሽሽ ብልሹ ምግባር ይዞ የሚመጣን የባለጌ ስብስብ የሃገራችንን መሬት እንዳይረግጥ እዛው ሳይነሳ ቪዛ እንዲከለከል መንግስት ከወዲሁ ግልጽ ያለ አቋሙን ሊያሳውቅ ይገባል።
ግብረ ሶዶምን ለመቃዎምና ይህችን ቅድስት ሃገራችንን እንዳይረግጥ ለማድረግ
Share
Share
Share
Via ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ገጽ
