
ከኢሳት ተገፍተው የወጡ ጋዜጠኞች መረጃ መለዋወጫ የፌስቡክ ገጽ እና የዩ ቲዩብ ቻናል ይፋ አደረጉ – መልእክታቸው ከዚህ በታች ተቀምጧል።
ለውድ ኢትዮጵያዊያንና ኢትዮጵያዊያት!!
በቅርቡ ከኢሳት ተገፍተን የወጣንና ለእውነትና መርህ የቆምን ጋዜጠኞች ከሕዝብ ጋር መረጃ የምንለዋወጥበት ኢትዮ 360 ሚዲያ (Ethio 360 Media) የተባለ የፌስቡክ ገጽ እና የዩ ቲዩብ ቻናል ይፋ ማድረጋችንን በአክብሮት እንገልጻለን። ይሕ የፌስቡክ ገጽ እና የዩ ቲዩብ ቻናል መረጃዎችን ወጥ በሆነ መንገድ የምናስተላልፍበት እንዲሁም የጋራ ድምጻችንን የምናሰማበት መሆኑንም በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን።
ማስታወሻ ፥- Ethio 360 Media በሚል የሰየምነውን የፌስቡክ ገጽና የዩቲዩብ ቻናል ላይክ እና ሼር በማድረግ ድጋፋቸሁን እንድትሰጡን እንጠይቃለን።
