2019-06-07

እስክንድር ነጋ ለሶስተኛ ጊዜ የታገደበት  መግለጫ በደህንነት ትዕዛዝ መሆኑ ታውቋል!!! * በዛሬው ዕለት የሰናይ መልቲ ሚዲያ ምስረታና የአክሲዮን ሽያጭ፤ ይፋዊ መግለጫ መንግስታዊ አፈና በድጋሚ ተካሂዶበታል!!! * ” ከደህንነት ተደውሎ ስለተነገረን አሁን መግለጫ መስጠት አትችሉም “ በድጋሚ ለሁልም ሚዲያ የተላለፈ ጥሪ ““አፈር ልሰንም ቢሆን የህዝብ ሚዲያ እንቋቁማለን!!! እስክንድር ነጋ” /// አዲስ የሳተላይት ቴሊቪዥን ጣቢያ ምስረታ ጋዜጣዊ መግለጫቦታ ፦ አዲስ አበባ ሂልተን ሆቴልቀን፦ አርብ ግንቦት 30/2011 ዓ.ምሰዓት፦ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓትሰናይ መልቲ ሚዲያ ፤ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ጋዜጠኛ እስክንድ ነጋ ፣ እንዲሁም እየታሰሩ እየተፈቱ ለህዝብ መሰዋዕትነት ሲከፍሉ በኖሩ አንጋፋ እና ወጣት የነፃው ፕሬስ ጋዜጠኞች አስተባባሪነት (ፕሮሞተርነት) የ24 ሰዓት ቲቪ ለመክፈት ህጋዊ የሆኑ ሂደቱ ተጠናቋል ።ትላንትና ፣ዛሬ እና ነገን እንደ-ድልድይ የሚያስተሳስር ፣ መረጃ ፣ ቁምነገር እና መዝናኛ ፕሮግራሞችን በላቀ ሁኔታ የሚያቀርብ ቲቪ፤ ህዝብ እንዴት የራሱ ማድረግ እንዳለበት በተመለከተ በሂልተን ሆቴልጋዜጣዊ መግለጫ ይስጣል።ይህ ጋዜጣዊ መግለጫ ለሁሉም የሚዲያ ተቋማት ክፍት ነው !ለበለጠ መረጃ በዚህ መልኩ የተዘጋጀ መጥሪያ የደረሳቸው ጋዜጠኞችና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሰአቱ ስፍራው ቢደርሱም የጠበቃቸው አሳፋሪ መንግስታዊ የመብት ጥሰት ነበር።     ለአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል በቀን 27/ግንቦት/2011 ዓ.ም በተፃፈ ደብዳቤ ፤ “ጌት አማካሪዎች” የንግድና ኢንቨስትመንት ማማከር ድርጅት፤ የሰናይ ቲቪ ምስረታ እና አክሲዮን ድርሻ ሽያጭን በተመለከተ ፤ለግንቦት 30/2011 ዓ.ም ከጠዋቱ 4 እስከ 6 ሰዓት ለሚደረገው ጋዜጣዊ መግለጫ የአዳራሽ ኪራይ የተጠየቀ ሲሆን ፤       ሂልተን ሆቴል በደብዳቤ ለቀረበለት ጥያቄ ግንቦት 28 ቀን 2011 ዓ.ም አወንታዊ ምላሽ በደብዳቤ በመግለጽ፣ ክፍያ እንዲፈጸም በጠየቀው መሰረት በዚው ዕለት 12995 ብር (አስራ ሁለት ሺህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና አምስት ብር ) ክፍያ ተፈጽሟል ።     ይሁን እንጂ በተገባው ህጋዊ ውል መሰረት፣ በዛሬው ዕለት ጥሪ የተደረገላቸው ጋዜጠኞች እና ጋዜጣዊ መግለጫ ለመስጠት የተገኙ የሰናይ መልቲ ሚዲያ መስራቾች ፣በቦታው ቢገኙም የተሳበው መግለጫ መስጠት አልተቻለም ።         ይህን ጉዳይ በተመለከተ የሆቴሉ የሽያጭ ክፍል እረዳት ስራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ ሰርጸወልድ ” ከሚመለከተው ክፍል ፍቃድ ካላመጡ መግለጫ እንዳይሰጡ” በማለት ከደህንነት ተደውሎ ስለተነገረን አሁን መግለጫ መስጠት አትችሉም ብሏል ። ለእኚህ ስራ አስኪያጅ የሰናይ መልቲ ሚዲያ መስራቾች “የሚመለከተው” አካል ማነው ?ይህን ማድረግ ከእኛ አይጠበቅም !ዝግጅታችን አጠናቀናል፣ ህጋዊ ውል ፈጽመናል ፣ መግለጫ እንድንሰጥ ወደ አዳራሹ እንድንገባ በሩ ይከፈትልን ፤ በማለት ጥያቄ ያቀረቡ ቢሆንም፤ አቶ አንተነህ የሆቴሉን ጥበቃዎችን በመጥራት የአዳራሹ በር በማዘጋት ፣” ይሄ ከእኔ አቅም በላይ ስለሆነ ፤ ጊቢውን ለቃችሁ ውጡልኝ ” ብለዋል ።       የሰናይ መልቲ ሚዲያ መስራቾች ይህ’ን መንግስታዊ የሚዲያ አፈና ፣እዛው በመረጃና በማስረጃ በሆቴሉ ቅጥር ግቢ ለተገኙ የሚዲያ ተቋማት በመግለጽ ፣ ግቢውን ለቀው ወጥተዋል ።      ከላይ ለተዘረዘሩት የውል ስምምነት ማስረጃ ከዚህ ጽሁፍ ጋር ተያይዟል ፣እኔ’ም በቦታው ስለነበርኩ እማኝነቴን እገልፃለው። ድል ለእውነተኛ ዴሞክራሲ !!! https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2647664685260883&id=924349197592449Filed in:Amharic