- በአንድ ሳምንት ውስጥ ለሁለት ጊዜ የእስክንድር ነጋ የጋዜጣ መግለጫ መርኃ ግብር በፖሊስ እንዲበተን ተደርጓል፣
- ሃሳብን የመግለጽ ነጻነት በገዥዎች ፍላጎት የሚሰጥና የሚከለከል እንጅ የዜጎች መብት አለመሆኑ አየታየ ነው፣
- አሁንም በሥልጣን ላይ ያሉት የሚፈልጉት አጨብጫቢዎችንና አሽቃባጮችን መሆኑ እየተረጋገጠ ነው፣
- በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚኖሩ የተወሰነ ቁጥር ያላቸው የኦሮሞ ብሔረሰብ አባላት ማሕበር አቋቁመው በከተማዋ ውስጥ አለን የሚሉትን መብት ለማስከበር በነጻነት ሲንቀሳቀሱ በእስክንድር ነጋ የሚመራው የባልደራስ ስብስብ ግን በጠላትነት ተፈርጆ እንዳይነቀሳቀስ የተለያዩ አፈናዎችና ጋሬጣዎች ተደቅነውበታል፣
- በእስክንድር ነጋ ላይ እየደረሰ ያለው አፈና ኢትዮጵያ ውስጥ ነጻ ምርጫ ኢህአዴግ እስካለ ድረስ እንደማይካሄድና ከገዥዎች ያለወገነ አስተሳሰብ እንደሚጨፈለቅ አመልካች ነው፣
ጋዜጠኛ አበበ በለው በዚህ ጉዳይ ላይ ያቀረበውን ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ውይይት ተከታተሉ።