June 8, 2019
Source: https://www.zehabesha.com/amharic/archives/95620
ከንቲባ ታከለ ኡማ “አዲስአበባ እንደ ስምዋ ገና ታብባለች። አዲስአበባ የሁሉም ኢትዮጵያዊ ከተማ ናት፣” ሲል ሰማሁ። በንድፈሀሳብ ደረጄም ቢሆን ይህ ቀና ሀሳብ ነው። እንድ እርምጃ ወደፊት መሄድ ነው። ከአዲስአበቤዎች ጋራ መቆም ነው።
.
አቶ እስክንድር ነጋና ከእሱ ጋራ የተሰበሰቡትም አዲስአበቤዎች የሚሉት ይህንኑ ነው። አቶ እስክንድርም በትህትና እና በሰላማዊ መንገድ የሚያስተጋባው ይህንኑ ሀሳብ ነው። ታድያ ለምንድነው አዲስአበቤዎች ስብሰባ እንዲያካሂዱ የሚከለከሉት? አስርም ሆኖ አስር ሺ ዜጎች ለምን ድምጻቸው አይሰማም? ሀሳብን በሀሳብ መሞገት ነው እንጂ ማፈን ወደፍንዳታ ያመራል። የታፈነ ሁሉ መፈንዳቱ የተፈጥሮ ህግ ነውና። ሁላችንም የታገልነው ኢትዮጵያውያን በነጻነት ተሰብስበው ሀሳባቸውን እንዲገልጹ ጭምር ነው። አለበለዛ ምኑን ለውጥ መጣ ይባላል?
.
ቀጥሎ ደግሞ የሚከነክነኝ አቶ እስክንድርና መሰሎቹ ሊያቋቁሙት ያቀዱት “ሰናይ፣” የተባለው ቴሌቭዥን ጉዳይ ነው። ኢሳት፣ OMN፣ አስራት፣ ወዘተርፈ የተባሉ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ተፈቅዶላቸው በሀገሪቱ ውስጥ ድምጻቸውን እያስተጋቡ ነው። እነአቶ እስክንድርም ይህንኑ ለማድረግ ወጥነው በኢትዮጵያና ሂልተን ሆቴሎች ስብሰባ ለማድረግ ሞክረው ሁለቴ ተከለከሉ። ለምን? ይህ ዲሞክራሲያዊ መብታቸው ኑው። መፈቀድ ይገባዋል። ይህ አካሄድ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ መንግሥት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ስለሚያሳድር እሳቸው እና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ባለስልጣናት አስበውበት የእነእስክንድርን ሀሳብ ባያፍኑት ይበጃል።
Sponsored by Revcontent