June 8, 2019

((((ምንሊክ ሳልሳዊ) በቡራዩ አስር ሺህ የሚደርሱ ቤቶችን ሊያፈርስ መዘጋጀቱን የከተማው ምክትል ከንቲባ አስታወቁ በቡራዩ የሚኖሩና መኖሪያ ቤታቸው ይፈርስባቹሃል በሚል ከፍተኛ ዛቻ በስብሰባ የተነገራቸው ነዋሪዎች ስንፈናቀል ከምትረዱን ሳንፈናቀል እርዱን።በማለት አቤቱታቸውን እያሰሙ ነው።

በአሸዋ ሜዳ አብድ ኖኖ ቀበሌ የስብሰባ አዳራሽ በተጠራው ስብሰባ ላይ የተገኙት የቡራዩ ከተማ ምክትል ከንቲባ ከ2005 ወድህ የተሰሩ ቤቶች በሙሉ እንደሚፈርሱ በመግለፅ ይህንንንም ተሞክሮ ከአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ እንደቀሰሙ በዝርዝር አስረድተዋል። ማፍረስ አዲስ ነገር አይደለም ያሉት የቡራዩ ከተማ ምክትል ከንቲባ ቤቶቹን ለማፍረስ አስፈላጊ ቅድመ ዝግጅት ማድረጋቸውን በቁጣ ተናግረዋል ሲሉ በስብሰባ ው ላይ የነበሩና በአከባቢው ለ አስራ አምስት አመት የኖሩት አቶ ቶፊቅ አብደላ በምሬት ተናግረዋል ሲሉ በስብሰባው ላይ ተሳታፊ የነበሩ ምንጮቻችን ገልጸዋል።

የቡራዩ ከተማ ምክትል ከንቲባ በማፍረሱ ሂደት ላይ ሕብረተሰቡ ከጎናቸው እንዲቆም ቢጠይቁም ከኦሮሞ ተወላጆች ከፍተኛ ተቃውሞ እንደገጠማቸው የገለጹት ምንጮች ያለፈው ጠባሳ ሳይሽር ዳግም ሌላ ቁስል ልታመጡብን ነወይ አብረውን ለሃያ አመታት የቆዩ ጎረቤቶቻችንን መንገድ ላይ ሲወድቁ ማየት አንፈልግም ሲሉ ተቃውሟቸውን የቡራዩ አከባቢ ተወላጆች አሰምተዋል።

ከህዝቡ ተቃውሞ መነሳቱን ሲመለከቱ እኛ ቤት እናፍርስ አላልንም በማለት ለማስቀየስ ሞክረዋል፤ በመጨረሻም ስብሰባ መጥተናል በሚል ሰበብ አብዛኛውን ሰው አስፈርመውታል ነገርግን ይህ ፊርማና ስብሰባ ቤት ለማፍረስ ህዝቡ ተስማምቷል ለሚል ፕሮፓጋንዳ እንደሚጠቀሙበት ምንም ጥርጥር የለውም ሲሉ ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።ከዚህ ቀደም በለገጣፎ በሱሉልታ የተሰራው ተመሳሳይ ስራ ሕዝቡን ስብሰባ መጥተናል ብህ ፈርም ብለውት ቤቱ እንዲፈርስ ተስማምቷል ብለው ማፍረሳቸው ይታወሳል።የቡራዩ ነዋሪዎች ነዋሪዎች ስንፈናቀል ከምትረዱን ሳንፈናቀል እርዱን።በማለት አቤቱታቸውን እያሰሙ ነው።(ምንሊክ ሳልሳዊ)