June 8, 2019
አማራ ማን ነዉ?
አማራ የኢተዮጵያዊነት ሌላዉ ገጽ ነዉ:: በመሆኑም ኢትዮጵያ ተብሎ ሲጠራ አማራዉ አቤት ይላል፡፡ አማራ ተብሎ ሲጠራ ደግሞ ኢትዮጵያዊነት ብቅ ይላል፡፡ ይህነን ሀቅ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ በኢትዮጵያዊነት የሚያምኑም ሆነ የማያምኑ ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ በዓለም ላይ ያሉ የሰዉ ዘሮች ለኢትዮጵያ ወዳጅም ጠላትም የሆኑ ሁሉ ጠንቅቀዉ ያዉቃሉ፡፡ለዚህም መረጃ ይሆን ዘንድ የዓለም ጸሀፊዎች ስለአማራዉ ኢትዮጵያዊነት፣ ስለ አማራዉ ለኢትዮጵያ ጸንቶ መቆም፣፡ አማራዉ ለኢትዮጵያ ጋሻና መከታ መሆን የዉጭ ወራሪዎች ኢትዮጵያን አጥፍቶ የየራሳቸዉን አገር ጥቅም በኢትዮጵያ ላይ ለመመሰረት በቅድሚያ አማራን ማጥፋት በሚል ከጻፉት ጸሀፊዎችና ጽሁፋቸዉ የሚከተለት ይገኙበታል፡፡
ፕሮፌሰር ሰብሰኪ የኢትዮጵያ ታሪክ በፋሺስት ጣሊያን ወረራ ወቅት በሚለዉ መጽሀፍ ጣሊያን ዓላማዋን ለማሳካት ዋና ግብ አድርጋ የያዘችዉ በኢትዮጵያ ዉስጥ ነገዶች በአንድ ላይ እንዳይኖሩ መበታተን በተለይም ለኢትዮጵያ አንድነት ዋና መሰረት ነዉ ያለችዉን የአማራ ነገድ በሌሎች ነገዶች ማሰጠላትና በጠላትነት አንዲተያዩ ማድረግ ይሀን ም እርዳታ በማድረግ ማጠናከር በሚል የጻፈዉ፤
አባይን ከምንጩ ለመቆጣጠር የሚፈልገዉ የግብጹ ተስፋፊ መሪ የመሃመድ አሊ የልጅ ልጅ ከዲቭ እሰማኤል ከሰዊዘርላንድ ተወላጅ ከወርልድ ሙዥንገር በተስጠዉ ምክር ግብጽን ለማስፋፋት ከተፈለገ ኢትዮጵያን መዉረርና እስልምናን ማስፋፋት፤ ካልተቻለም እድሜልኳን እየተናኮረች እንድትኖር በአማራዉ ነገድ ላይ የማጥላሊያ ዘመቻ በማካሄድ ከሌሎች ነገዶች ጋር አናክሶ እነዲኖሩ መድረግ የሚል ነዉ፡፡ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ግብጽ በኢትዮጵያ ላይ ተደጋጋሚ ወረራ አድርጋለች፡፡ የቀጥታዉ ወረራ አልሳካላት ሲል ለኢትዮጵያ ወራሪና ተቃዋሚ የምትፈጥረዉም የተፈጠረዉንም የምትረዳዉ ግብጽ ሆነች፡፡
ሮማን ፐርቻስካ በአዉሮፓዊያን ላይ የሚሰነዘረዉ ጸረቅኝ ገዥነት ለመከላከል በኢትዮጵያ ላይ አርምጃ መወሰድ አለበት በተለይም በአማራዉ ላይ የአማራዉ ገዥ የሚኒልክ ሥራ የአዉሮፓ ተቋማትን ለማጥፋት የተቃጣ አካሄድ ነዉ፡፡ በነጭ ዘር ላይ ከፍተኛ ጥላቻ አላቸዉ፡፡ የመጨረሻ ግባቸዉ ለአፍሪካዊያን የተሸለና ምሳሌ ሁኖ ለመገኘት ነዉ፡፡
በሰኔ ወር 1935 ዓ.ም የአማራዉ ገዥ ኃይለ ሥላሴ ለጦር አለቆቻቸዉ የአፍሪካ ከፍተኛ ንጉሥ እኔ ነኝ ለዓለም ጥቁር ህዝቦች ገና ነጻ ያልወጡትን ጨምሮ ብለዋል፡፡ ለማተን ለተባለዉ ጋዜጣ በሰጡት ቃለ ምልልስ በቁርአን ላይ መሀመድ እንደአስቀመጡት ኢተዮጵያዊያን አስተናግደዉናል ብለዋል፤ ሰለዚህ ሙስሊሞች በፈለግን ጊዜ ሊረዱን ይገባል የሚል መልእክት አሰተላልፈዋል ወዘተ በማለት ኢተዮጵያ በአማራዉ አማካይነት በምእራባዊያን አልገዛ ማለቷን ሮማን ፐርቻስካ አበክሮ በዝርዝር ጽፎታል፡፡
ሮማን ፐርቻስካ ኢትዮጵያ የባሩድ በርሚል በተሰኘዉ መጽሀፉ ገጽ ሶስት ላይ ምእራባዊያን ወገኖቼ ስሙኝ በምስራቅ አፍሪካ በምትገኘዉ ኢትዮጵያ ዉስጥ አንድ አማራ የሚባል ነገድ አለ፤ ይህ ነገድ እኛ ምእራባዊያን በአፍረካ በምናደርገዉ የመስፋፋት ፖሊሲ ትልቁ እንቅፋት ነዉ፡፡አማራ ከተደራጀ እንኳን ለአፍሪካ ለኛም ትልቅ ስጋት ነዉ፡፡ እየእዳንዱ ምእራባዊያን አገር የሚከተለዉ ፖሊሲ ከዚህ አንጻር መቃኘት አለበት ብሎ በመጻፍ ለምእራባዊያን አሰራጨ፡፡
ሩደልፍ የተባለ ጸሀፊ “አማራዉ ለኢትዮጵያ የቆመ ሀይል ነዉ፤ አማራዉ እንዳይደራጅ ጠብቁት፤ አማራ ለጊዜዉ የተሸነፈ መስሎ እገቱን ቢደፋ ቀን ጠብቆ መነሳቱ አይቀርም፤ የሞተ አማራ አይነሳም ብሎ ማመን እንጂ የተዳከመ አማራ አይነሳም ብሎ ማመን ቂልነት ነዉ” ሲል ጽፏል፡፡
የምእራባዊያንን ዓላማ ለማሳካት አማራን ለማጥፋት በመርሀ ግብር ነድፎና እቅድ አዉጥቶ በማጥፋት ላይ የሚገኘዉ ፡የአማራዉ ቀንደኛ ጠላት መለስ ዜናዊ አማራ ኢትዮጵያዊ መሆኑን እንዲህ ሲል ምሰክረነቱን ሰጥቷል፡፡አማራ ኢትዮጵያዊነት ዘልቆ የተዋሀደ እናከደመነፍሱ ጋር የተሳሰረ ነዉ፡፡ይህነንከሀዝቡ ስነ አእምሮ ነጥሎ ለመጣል በዘር፣ በቋንቋ፣ማደራጀት እና በዚሀ ዓላማ የሚመሩ ድርጅቶችን መፍጠር ነዉ፡፡ብሎ ኢትዮጵያን ለማጥፋት በቅድሚያ አማራን ማጥፋት ነዉ ብሎ ሰራበት ሲሞትም የመለስ እራይ እና ዉርስ በሚል እንዲሰራበት ተናዞ ይኸዉና እስከ አሁንም እየተሰራበት ነዉ፡፡ ወደፊትም በሙታን መንፈስ እየተመራ ሊሰራበት ታቅዷል፡፡
በአጠቃላይ ስለኢትዮጵያ መጥፋት የሚፈልጉና ለማጥፋትም የጥፋት ዘዴ የሚፈጥሩት የምእራባዊያን ጸሀፊዎች ኢትዮጵያን ለማጥፋት ቅድሚያ አማራዉን ማጥፋት ነዉ እያሉ ሲጽፉ፣ እየዞሩ ሲያሰተምሩ በተቃራኒዉ የሚያስረዳዉ አማራና ኢትዮጵያዊነት ድርና ማግ ሁነዉ ኢትዮጵያን ጠብቀዉ መያዛቸዉን ነዉ፡፡
ከዚህ ላይ አማራዉ ልብ ሊለዉና ሊያጤነዉ የሚገባዉ በወያኔዉ መሪ መለስ የወጣዉ አበዮታዊ ዲሞክራሲ የሚለዉ ፖሊሲና ለዚሁ ማስፈጸሚያ የተዘጋጀዉ ሰነድ ወይም ህገ መንግስት አማራን አጥፍቶ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ተነድፎ እየተሰራበት የቆየ እየተሰራበትም የአለና ወደፊትም ሳይለወጥ ሊሰራበት የታቀደ መሆኑን ነዉ፡፡
የአማራዉ ህልወና ኢትየጵያ አንድነት ድረጅት አገርን ለማጥፋት አልሞና አቅዶ በመርሀ ግብር ነድፎ ለማጥፋት በተሰለፈዉ የወያኔ መሪ የወጣው አበዮታዊ ዲሞክራሲ ፖሊሲና የማሰፈጸሚያዉ ህገመንግስት በጥገና ሳይሆን በመሰረታዊ ለዉጥ እንዲተካ ከሚፈልጉ ኢትዮጵያዊያን ጎን ተሰልፎ ይታገላል፡፡
ሙላት በላይ
ቁጥር 3 ይቀጥላል Sponsored by Revcontent