June 12, 2019
Sourc: (ኢትዮ 360 )

በኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን በዝምታ እንደማያልፋቸው የዲሲ ግብረ ሃይል አስታወቀ
(ኢትዮ 360 )
በኢትዮጵያ እየተፈጸሙ ያሉ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ከዚህ በኋላ በዝምታ እንደማያልፍ የዲሲ ግብረ ሃይል አስታወቀ።
ግብረ ሃይሉ ባወጣው መግለጫ እንዳለው ለረጅም ጊዜ የተቆመለትና ትግል ሲደረግ የቆየበት የሃሳብ ልዩነትን የማክበር ጉዳይ በተደጋጋሚ ሲጣስ ቆይቷል።-አሁንም በመጣስ ላይ ነው።በተደጋጋሚ እንደ ሃገር ለሚከሰቱ ችግሮች ስልጣን ላይ ያለው አካልም ምንም አይነት ምላሽ መስጠት አለመቻሉ በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመኔታ እያሳጣው መምጣቱን ይገልጻል መግለጫው።
እንደ ቀድሞው አስተዳደር በሃገር ውስጥ ባሉ ተቋማት ብቻ ሳይሆን በውጭ ኤምባሲዎች ጭምር ያለው ምደባ በአንድ ቋንቋ ተናጋሪዎች እንዲሞላ መደረጉ አሳሳቢና ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው ሲል የዲሲ ግብረ ሃይል በመግለጫው ላይ አስፍሯል።መንግስት ችግሮች ከመፈጠራቸው በፊት የቅድመ መከላከል ስራ አለመስራቱ ብሎም ችግሮች ሲከሰቱ አስቸኳይ መፍትሄ አለመወሰዱ የለውጡን ሒደት ግራ የሚያጋባ አድርጎታል ብሏል።
በሰብአዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ላይ በተደጋጋሚ የሚደርሰው ወከባና እንግልት፣እንዲሁም የአደባባይ የግድያ ዛቻ ግብረ ሃይሉ በፍጹም የማይቀበለው ተግባር መሆኑን ገልጿል።በአንጻሩ ደግሞ ከ17 ጊዜ በላይ የህዝብ ባንክ የዘረፉ፣ህዝብን እርስ በርስ ለማጋጨት የሚንቀሳቀሱ አክቲቪስቶችም ሆኑ ቡድኖች በዝምታ ሲታለፉ ሲታይ መንግስት ሆን ብሎ በራሱ ላይ ጫና እንዲፈጠር ያደረገው ነው የሚል እምነት እንዳለው የዲሲ ግብረ ሃይሉ በመግለጫው አስቀምጧል።
ይህ ህገ ወጥ ድርጊት በአፋጣኝ ካልታረመና ወንጀለኞቹ በአስቸኳይ ለፍርድ የማይቀርቡ ከሆነ ህዝብን በመንግስት ላይ ጥርጣሬ እንዲጨምር ከማድረጉም በላይ ግብረ ሃይሉም እንዲህ አይነቱን ዝምታ በቸልታ የማያልፈው