Facebook logo

የማሕበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ሆነ ብለውም አልያም በስህተት የሚያሰሯጯቸው መረጃዎች በሌሎች ተጠቃሚዎች ላይ ቀጥተኛ የሆነ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ።

በኢትዮጵያም ፌስቡክን በመጠቀም የሚሰራጩ አንዳንድ መረጃዎች በሌሎች ተጠቃሚዎች ላይ ጉዳት ሲያስከትሉም ተስተውሏል።

የማህበራዊ ሚዲያ አውታሩ ፌስቡክም መሰል መረጃዎች በሌሎች ላይ የሚያሳድሩትን ጫና ለመቅረፍ በማሰብ ማንኛውም የፌስቡክ ተጠቃሚ በገፁ ላይ የሚመለከታቸው መልዕክቶች (Facebook posts) በሌሎች ሰዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ ይችላሉ ብለው ከገመቱ ጉዳዩን ለፌስቡክ ሪፖርት የሚያደርጉበት ቀላል አማራጭ አቅርቧል።

ፌስቡክና ትዊተር ሐሰተኛ አካውንቶችን ሊያጋልጡ ነው

በሃሰተኛ ዜናዎች “የሞቱ” የኪነጥበብ ሰዎች

ለመሆኑ በሰዎች ላይ ጉዳት ሊያስከትሉ የሚችሉ የፌስቡክ መልዕክቶች የትኞቹ ናቸው?

የሚከተለው ይዘት ያላቸው መልዕክቶች በተጠቃሚዎች ላይ ቀጥተኛ ጉዳት ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ፌስቡክ ሪፖርት ሊደረጉልኝ ይገባል ይላል። መልዕክቶቹ በጽሁፍ፣ በፎቶ ወይም በቪዲዮ ሊቀርቡ ይችላሉ።

‘ሃሰተኛ ዜና ‘፡ የኢትዮጵያ የማሕበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ስጋት?

አይሸወዱ፡ እውነቱን ከሐሰት ይለዩ

ከላይ የተጠቀሱትን አይነት ይዘት ያላቸውን የፌስቡክ መልዕክቶች እንዴት ሪፖርት ማድረግ ይቻላል?

ቀላል ነው።

Facebook

ለምሳሌ በምስሉ ላይ የሚታየው መልዕክት ይዘት በፌስቡክ ተጠቃሚዎች ላይ ጉዳት ያደርሳል ብለን እናስብ።

ይህን መልዕክት ለፌስቡክ ሪፖርት ለማድረግ ከመልዕክቱ በስተቀኝ አናት ጋር የሚገኙ ••• (ሶስት ነጥቦች) መጫን። ሶስቱን ነጥቦች ስንጫን አራት አማራጮችን ይሰጠናል። ከዚያም የመጨረሻውን አማራጭ ማለትም ”በመልዕክቱ ላይ አስተያየት ይስጡ” (Give feedback on this post) የሚለውን ይጫኑ።

Facebook

”Give feedback on this post” የሚለውን ሲጫኑ ከላይ የሚታየውን አይነት ሌላ አማራጭ ይሰጥዎታል።

ለምሳሌ የተመለከቱት የፌስቡክ ፖስት ወይም መልዕክት ሐሰተኛ ዜና ከሆነ፤ False news የሚለውን ይጫኑ። ከዚያም ጉዳዩን ፊፖርት በማድረግዎ ከፌስቡክ የምስጋና ምላሽ ያገኛሉ።

ይህን የፌስቡክን ስርዓት በመጠቀም በሰዎቸ ላይ ሊደርሱ የሚችሉ አሉታዊ ተጽእኖዎችን መቀነስ ይቻላል።