June 13, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/124384

ህወሃት ጉያ ውስጥ የክፋትና የመሰሪነት ጡጦ ሲጠባ ያደገው አብይ አህመድ በህዝባዊ አመጽና ለረዥም ዓመታት በተደረገ ሰላማዊ ትግል የሥልጣን ማማ ላይ ከተፈናጠጠ በኋላ በአፈ ጮሌነትና በማጭበርበር በርካታ ቁጥር ያላቸውን ኢትዮጵያዊያንን እንዳደነዘዘና እንዳፈዘዘ ይታወቃል። ብዙ ሽህ ቁጥር ያለውን የፌዴራል መንግስትን ጦር ሰራዊት፣ ታንኩን፣ የጦሩን አውሮፕላኑና መድፉን በእጁ ቢያስገባም የህወሃትን ወንጀለኞች እንደ ጌታቸው አሰፋ አይነቶቹን ለፍርድ ለማቅረብ ወኔው የከዳውና የተልፈሰፈሰው አብይ አህመድ በሰላማዊ መንገድ የህዝብን ጥያቄ አንስቶ የተገፋውንና የተረገጠውን የአዲስ አባባ ህዝብ ብሶት በማሰማቱ ምክንያት ከአስኪሪቢቶና ወረቀት ሌላ ምንም የሌለውንና በሰላማዊ ትግልና በጋዜጠኛነቱ ዓለም የተመሰከረለትን እስክንድር ነጋን የወገንቡ ቅማል ሆኖበት አላስቀምጥ አላስቆም ብሎት እንደ አህያ እንዲያናፋ አስገድዶታል። እስክንድር ነጋ ለበርካታ ዓመታት ለዲሞክራሲ፣ ለእኩልነትና ለአንድነት መስፈን በህወሃት እስር ቤት ሲሰቃይ በነበረበት ጊዜ አብይ አህመድ የህወሃትን ሹመት ተቀብሎ የስለላ መስሪያ ቤት በመምራት ንጹሃንን እየሰለለ ለመከራ አሳልፎ ይሰጣቸው እንደነበር እራሱም ቢሆን የሚክደው ሃቅ አይደለም። በነዚያ የአፈናና የስቃይ ዓመታት እስክንድር ነጋ ህጻን ልጁንና ባለቤቱን ለመከራ አጋልጦ እሱ እስር ቤት ውስጥ እድሜውን አጋምሶታል። አብይ አህመድ ይሉኝታ የሌለውና በጭብጨባ ብዛት ናላውን የሳተ በመሆኑ ነው እንጅ እስክንድር ነጋ ላይ አፉን የሚከፍትበት የሞራልም ሆነ የግብረገብ ብቃት የለውም

አብይ አህመድ ሰኔ 16, 2010 አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በደረሰበት የግድያ ሙከራ የህይወት መስዋዕትነት የከፈለለትንና አሁን ለመጣው ለውጥ ለብዙ ዓመታት  ምርጫ 97ን ጭምር ከፍተኛ የህይወት መስዋዕትነትን የከፈለውን የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ ክህደት ፈጽሟል። የአዲስ አበባን ህዝብ በጎሳ ጥላቻ ላበዱና በጠራራ ጸሃይ ባንክ ለሚዘርፉና የንጹሃንን ደም ለሚያፈሱ ወሮበሎች አሳልፎ ሰጥቶታል። አህይ አህመድ በተለያዩ ቦታዎች የዘር ተኮር ጭፍጨፋ የሚፈጽሙና ቤት የሚያቃጥሉና የሚያፈርሱ “ጊዜው የኛ ነው” የሚሉ እጅግ ጥቂት ቁጥር ያላቸው በኦነግ ስም የሚንቀሳሱ ሽፍቶችን መቆጣጠርና ለፍርድ ማቅረብ ተስኖት አገር እያታመሰና በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህጻናት፣ ሴቶች፣ አቅመ ደካቦሞችና አካለ ስንኩላን ከመኖሪያ ቀያቸው ተፈናቅለው ዋይታ በሚያሰሙበት ወቅት አብይ አህመድ ሁሉን ነገር እርግፍ አድርጎ ትቶ ጉልበቱንና ኃይሉን እስክንደር ነጋ ላይ አሳርፎ አያስፈራራውና እያንገላታው ይገኛል። በአንጻሩም “ሆሮምሳ ፊንፊኔ” የተባለውን ህገ ወጥ ቡድን የአዲስ አበባ ነዋሪ ያልሆኑ ሰዎችን ህገወጥ መታወቂያ እየሰጠ የነዋሪዎችን ቁጥር ለማዛብባት ወንጀል እንዲፈጸም እያስደረገ ይገኛል።

ውስጥ አወቆች እንደጠቆሙት አብይ አህመድ አክሱም ከተማ ውስጥ ከሁለት ቀናት በፊት ባደረገው ጉብኝት ከህወሃቶች ጋር “የጋራ ጠላታችን” የሚሉት እስክንድር ነጋ ላይ ለመዝመት ስምምነት እንዳደረገ ታውቋል። አብይ አህመድ ህወሃት በሽህ የሚቆጠሩ ንጹሃንን ያሰቃየበትንና ለሞት የዳረገበትን “አከልዳማና” “ጀሃዳዊ ሀረካት” ትያትሮች በመኮረጅ እስክንድር ነጋ ላይ የተፈበረከ የውሸት መረጃ በማሳየት እስር ቤት ሊያስገባው እንደሆነ በስውር የወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ይህም ሁኔታ አይናቸው እያየና ጆሯቸው እየሰማ በተለያ ጥቅም በመደለል አብይ አህመድ የአዲስ አበባ ህዝብ ላይ የሚፈጽመውን ወንጀል ሲያስተባብሉ የነበሩ አድር ባዮችንና ሆዳሞችን እንደሚያስፍራቸውና እንደበፊቱ በየሚዲያው እየወጡ ለአብይ ከበሮ ሰደልቁ ህዝብ ዝም ብሎ እንደማይሞኝላቸው ለመገመት አያዳግትም።