June 13, 2019

ይሄን ጥያቄ የምጠይቀው አንድ እንደዘመኑ አገላለጽ የተፎካካሪ ቡድን ሊቀመንበር ስለራሱ ቡድን መርህና ፖሊሲ በአገኘው አጋጣሚ ያስተዋውቃል እንጂ የራሱን ተፎካካሪ (ሊያውም ጤነኛ ቢሆን እኮ ጥሩ) ደግፉ እያለ እየዞረ አይሰብክም፡፡ እኔ በብርሀኑ ከጀምሩም ደስተኛ ያልሆንኩ ሰው ነኝ፡፡ በእኔ ምልከታ በአርበኞች ግንቦት 7 በሚባለ ቡድን ውስጥ ሲሰራ የነበረው ብዙው ቁማር እንደነበር ነው የሚገባኝ፡፡ ስለዚህ ጉዳይ ቀደም ብዬ ገልጬዋለሁ፡፡ አሁን ስለማይጠቀም ወደዛ አልሄድም፡፡ ችግሩ ግን እዛ የነበረው ችግር አሁንም እየተከተለን መሆኑ ነው፡፡ የብርሀኑ ነጋ ዓላማ ግን ምንድነው? እውን ኢትዮጵያዊነት ወይስ እንደምንም በሕይወቱ አንዴም ቢሆን እንኳን ሥልጣን ላይ መድረስ፡፡ እኔ የማስተውለው ጥሩ አደለም፡፡ ለማንኛውም አሁንም ኢዜማ የተባለው ቡድን ራሱን ቢያስተካከል ጥሩ ነው፡፡ የአብይ ደጋፊ ለመሆን ተፎካካሪ ብሎ ሌላ ቡድን ማቋቋም ምን አስፈለገ፡፡

ዛሬ የለውጥ ኃይል ነኝ ያለውን ቡድን እኮ እኔ ብርሀኑና ሌሎች ሁሉ እስከመጨረሻው እየተቃወሙ በነበረበት ወቅት በጣም አጣብቂን በሆነበት ሁሉ በሙሉ ተስፋና ግልጽ በሆነ አቋም የደገፍን ብዙዎች አለን፡፡ ድጋፋችን ለዓላማ አገርና ሕዝብን ወደ ተመኘነው ነጻነት ለማድረስ እንጂ የግል ጥቅም ፍለጋ አደለም፡፡ ዛሬ ብዙዎች የሆነች ለራሳቸው የግላቸውን ጥቅም ስላገኙ ከተቃዋሚነት ተገልብጠው ከደጋፊም አልፈው ካድሬ ሆነዋል፡፡ ብርሀኑም ሆነ ሌላው ከእነዚህ እንደ አንዱ ሆነው እንጂ አሁን ያለው እውነት አብይንና ራሱን የለውጥ ኃይል ነኝ እያለ ያለውንና ብዙ ችግሮችን እየፈጠረ ያለውን ለመደገፍ ምክነያት የለንም፡፡ እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ፡፡ አብይንም ሆነ ቲመ ለማ የተባለውን ቡድን ዛሬ ተገልብጠው እነሱን አትንኩብን የሚሉትን በዛ ቀውጢ ወቅት የሚሰነዝሩትን መርዛቸውን ለማምከን ብዙ ለፍተናል፡፡ ዛሬ ለግላቸው ስለተሳካላቸው አገርና ሕዝብ ግን ከቀደመውም በከፋ ችግር ውስጥ ገብቶና ግልጽ የሆነ ውንብድና እያየን የምንደግፍበት ሕሊና የለንም፡፡ ሊያውም የተፎካካሪ ቡድን ሳንሆን በንጹ የዜግነት ኃላፊነታችን፡፡ ዜጎች በየቦታው መፈናቀላቸውን እንደ ችግር አይተን ዝም ስንል ማንነትን ኢላማ አድርጎ ራሱ መንግስት ነኝ ያለው የአብይ ኦፒዲ ቡድን የብዙዎችን ቤት አፍረ ያፈናቀለ እኮ ነው፡፡ ብርሁኑ ነጋ ይሄ ይገባው ይሆን? እናት በወለደችበት ቤቷ ፈርሶ ጉዳና ላይ የተጣለቸው በማን ነው? ሕጻናትና ታዳጊዎች ከትምህርት ቤት ሲመለሱ ቤታቸውን አፍርሶ የጠበቃቸው ማን ነው? ብርሀኑ ነገጋ ከ60ዎቹ ጀምሮ በፖለቲካ ድራማ ውስጥ አለ፡፡ ግን ስለዚህ ጉዳይ ይገባዋል? ዜጋ ማለትስ ይገባዋል? በየትኛውም መስፈርት ሕገወጥ እንኳን ቢሆን ሲጀምር ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የማንንም ነብረት አደለም በዶዘር ግቢው አጠገብ መድረስ ባልተቻለ፡፡ ሲቀጥል ፍርድ ቤት እንኳን ቢፈርድ እንዲህ የወንበዴ አይነት የሰዎች ቤት በዶዘር የማፍረስ መብት ሊኖረው ባልቻል፡፡ መንግስት የሚለው ቢገባው ግን የሆነውም ቢሆን ሕጻናትንና የቤቱን ሰው ሁሉ በቂ የሆነ መጠለያ ሳያዘጋጅ ይሄን ድርጊት ባለሰበው፡፡ ይሄን እኮ ነው የማይገባችሁ፡፡ ዜግነት ማለት ለአጠፋ ሰው በሕግ አግባብ ይቀጣል እንጂ ከእነ ቤተሰቡ አፈናቅሉ ሜዳ ላይ መጣል አደለም፡፡ በዜግነት ሥም አትቀልዱ፡፡

ሌላው አዲስ አበባ ላይ ኮነደሚኒየም የደረሳቸውን የተደረገው ድርጊት፣ ቆይቶም ራሱ የአብይ ቡድን ያወጣው መግለጫ፣ በግል በውስት ብዙ አምነንው የነበረው ለማ ሳይቀር የተናገረው ንግግር፡፡ ዛሬም ድረስ በይፋ እንደልባቸው ሕዝብንና አገርን እያሸበሩ በከተማ ጭራሽ በፖሊስ ታጅበው የሚሄዱ አለሌዎችን አሰማርቶ እያየን፣ የመንግስት ወሳኝ መዋቅሮች በተለይም የገንዘብ ምንጮችን በኦነጋውያን እያስያዘ እያየን ነው፡፡ ለመሆኑ ብርሁን ይሄ አይታየውም፡፡ እስኪ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ተመልከቱ ሥርዓስኪያጁ በኦሮሞነት ከአዋሽ፣ ምክትሉ በኦሮሞነት ከኦሮሚያ ኢነተርናሽናል ባንክ ሌሎቹም ከ8 ሥራ አስፈጻሚ ቢያንስ 5 ኦሮሞ፡፡ አስተውሉ አዋሽና ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ የንግድ ባንክ ተፎካካሪ ናቸው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች በነበሩበት ባንክ አክሲዮን አላቸው፡፡ በዚህ ላይ በኦሮሞ የዘረኝነትና ጣላቸው ፖለቲካ ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከሚሰሩ ናቸው፡፡ እና እነዚህ ስብስቦች ናቸው ዛሬ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን በዋናነት የሚመሩት፡፡ በተግባርም እንዳየንው እያዘረፉት ያሉት፡፡ በእርዳታ ሥም ገንዘብ እያወጡ የሚያድሉት፡፡ ልብ በሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የእርዳታ ድርጅት አደለም፡፡ ሙሉ በሙሉ የመነግስት ተቋም ነው፡፡ እርዳታው እንኳን ቢያስፈልግ መንግስት ከባንኩ የሚያገኘውን ገንዘብ በጥናት ለተፈለገው አገልግሎት ያውለዋል እንጂ በሥራአስኪያጁ ልግስና እየተነሳ የሚታደል አደለም፡፡ ብርሀኑ ነጋ ኢኮኖሚስት ነው ይሄ አይገባውም፡፡ ከዚህ በከፋ ግን ለአገር ጠላት ለሆኑ ገንዘብ በዝርፊያ ሥም እያስተላለፈ ነው፡፡ በተመሳሳይ ገቢዎች አካባቢ ያለው ሁኔታ ይሄው ነው፡፡

ሌላው ዜጎች ያልሆኑ በአገሪቱ እንደልባቸው ችግር እየፈጠሩ እንደሆነና አንዳንዶችም በሚታወቅ ቦታ በመንግስት ኃላፊነት በኦሮሞነታቸው ተመድበው እየሰሩ ነው፡፡ ይሄን ሊጠይቅ የወደደ አንደም ጋዜጠኛ የፖለቲካ ቡድን አላየሁም፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ምን አልባትም ዛሬ ኢትዮጵያ ውስጥ በዋናነት ብጥብጥ እየፈጠረ ያለው ጀዋርን ጨምሮ ብዙዎች ዜግነታቸው ሌላ ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ፡፡ እንግዲህ የዜግነት ጉዳይን በዜጎች ቁርጠኝነት እንጂ በአድር ባዮች እንማይሳካ አይተናል፡፡ እንጂማ ዜጋ ያልሆ በሌላ አገርና ዜጎች ሊያውም በእኩይነት ጣልቃ እየገባ በ24 ሰዓት ከአገር እንዲባረር ካልሆነ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ዋናው የመንግስት ኃላፊነት ነበር፡፡ የጥምር ዜግነት ይልልኛል አንዳንዱ፡፡ አለሌና ሥርዓት የማያውቅ በምን መስፈርት ነው የሁለት አገር ዜጋ ሊሆን የሚታሰበው፡፡ ከአንዱ አገር ወንጀል እየሰራ ሌላው አገር እንዲደበቅ ካልታሰበ፡፡ ይልቁንስ ይሄ ጉዳይ የምትቹሉ ካላችሁ ኢትዮጵያ ውስጥ የሌላ አገር ዜግነት ይዘው ዋና የብጥብጥ ሴራን እያሴሩ ያሉ በተለይ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ለራሷ ለአሜሪካ አስፈላጊውን መረጃ በማቅረብ ዜጎቿን ሥርዓት እንድታሲዝ ነው፡፡ አገሮች ዜጎቻቸው በዲፕሎማሳዊ ተልዕኮ አስተዋጾ እንዲያደርጉላቸው እንጂ በውንብድና ሌላ ተወልደንበታል በሚል ሌሎች ሕዝቦች ላይ ወንጀል እንሚሰሩ በውል ቢያውቁ ትልቅ እርምጃ ይወስዳሉ፡፡ ይሄ ትልቅ ከአገር ደህንነትና ልዕልና ጋር የተያያዘ ነውና፡፡ ለምሳሌ ኤርሚየስ ማዴቦ አሜሪካዊ እንደሆነ ነግሮናል፡፡ ታዲያ ስለኢትዮጵያ ምን አገባው? በኢትዮጵያ ጉዳይ እንዴት እንደነዚህ ያሉ ሰዎች ችራሽ ዋና ይሆናሉ፡፡ ይሄ እኮ ነው ሰዎች የማይረዱት እነ አብይ ሕዝብንና አገርን የመምራት መሠረታዊ ብቃት የጎደላቸው እንደሆነ የሚያሳየው፡፡ እንጂማ አንድም የሌላ አገር ዜጋ የሆነ በኢትዮጵያ ጉዳይ አያገባህም ተብሎ ሲተላለፍ በ24 ሰዓት ጊዜ ውስጥ ከአገር እንዲወጣ ማስገደድን ጭምር እርምጃ መውሰድ ነበር፡፡ አገርና ዜግነት በጽኑ መርህ እንጂ አቀውቅሀለሁ አውቅሻለሁ በሚል አደለም፡፡

ስለዚህ ብርሁኑ ነገጋ የአብይ ደጋፊ ለመሆን ተጨማሪ ቡድን መቋቋም አያስፈልግም፡፡ ኦፒዲ ወይም አንዱ ውስጥ እንምንም ተለማምጦ ቦታ መያዝ እንጂ፡፡ የዜግነትን ዋጋ አታርክሱ፡፡ እስክንድር ነጋ ብቻውን የዚህን ያህል እየታገለ ያለውን አንዳችሁም ለተሰየማችሁበት የዜግነት ቡድን ላላችሁት ስትሉ እንኳን በአፍ እንኳን በዜጎች ላይ እየሆነ ያለውን ሁሉ ዝም ማለት ሳያንሳችሁ ጭራሽ ሌላውን ገዳይህንና የሚዘርፍህን ደግፈው የካድሬነት አገልግሎት መስጠት ጀመራችሁ፡፡ አዝናለሁ፡፡ ምርጫ ቢኖር የቀረው ጥቂት ጊዜ ነው፡፡ በዚህ ወቅት ከአብይ ቡድን የምትለዩበትን መርህና ፕሮግራማችሁን በይፋ ለሕዝብ የምታቀርቡበት በሆነ፡፡ አሁን በምናየው አንድም ተቃዋሚ የለም፡፡ ሁሉም የአብይ ጭፍራ ሆኗል፡፡ እንግዲህ የሚቀጥለው ምርጫ እውን ከተደረገ አስቂኙን ድራማ ልናይ ነው፡፡ ግን ብርሀኑ ነጋ ለዜጋ አሳቢ ቢሆን ለምን ራሱን ቢያንስ አሁን ከሚመራው ቡድን ከሀላፊነት አላገለለም? በአጠቃላይ ጥሩ አደለም፡፡ አብይን በዜግነትና በኢትዮጵያዊነታችን ደግፈንዋል፡፡ እስከሞት ስሱ መሥዋዕት የሆኑ አሉ፡፡ ለዚህ የዜጋ ፍቅር ነው ዛሬ አብይ ከአራጆች ጋር ተባብሮ የተገኘው፡፡ ቢያውቅበትማ በዚህ አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ብዙ መሠረቶችን በኖረ፡፡ ብዙዎች ከሚታሰበው በላይ ተነሳስተው ባሉበት ሁኔታ ነው ተስፋውን ሁሉ ውሀ የቸለሰበት፡፡ ስለዚህ ብርሀኑ የግል ፍላጎቱ ስለተሳካ መደገፍ መብቱ ነው፡፡ የእኛ ችግር የግል ጉዳይ ሳይሆን የአገርና ሕዝብ ጉዳይ ነው፡፡ አሳዛኙ ነገር ወደፊትም የሚታመን መሪ እንኳን ቢመጣ ማመን እንዳይኖር ነው ያደረገው የአብይ ቡድን፡፡  እንግዲህ የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ መልካም በመስራት ለራስም ጥሩ ሆኖ አገርና ሕዝብንም ጠቅሞ በሰውም በእግዚአብሔርም መወደድ ሲቻል ምርጫቸውን ሴራና ተንኮል ያደረጉ እድሜ ልካቸውን ከሴራ ውጭ አማራጭ እንዳለ አይታያቸውም፡፡ እነ አብይን ተጸጽተዋል ብሎ ሕዝብ ደገፋቸው እንጂ ለ27 ዓመት በኖረው ሴራ ውስጥ አገልጋይና የሴራ አቀናባሪም እንደነበሩ ሕዝብ አላጣውም፡፡ ዛሬ በወያኔ ማሳበብ አይቻልም፡፡ የሕዝብ ድጋፍን ለማግኘት በካድሬነት የት እንደሚዘለቅ እንጃ ለ50 ዓመት ካድሬን የመረረው ሕዝብ ነው፡፡ አብይና ቡድኑ በይፋ ሕዝብን ይቅርታ ጠይቀው በተግባር የሚታየን ነገር ማሳየት ቢችሉ ሕዝብ በደገፋቸው፡፡ በየቀኑ ሴራውንና አስመሳይነቱን እየጨመሩበት አይሳካላቸውም፡፡ አንድ ግለሰብ እስክነድር መሠረታዊ የሕዝብ ጉዳይ ስላነሳ ያልከው ትክክል ነው፡፡ ብሎ ሆኔታዎችን እንደማረም ይሄው የተራ ወንበዴ ሴራ ሲያሴሩ እናያለን፡፡ የሒልተኑ ሰውዬ እኔ ነኝ የከለከልኩት ሲል በሕግ ምን ማለቱ እንደሆነ እንኳን አያስተውልም፡፡ ኦሮሞነቴ ካለልኝ በሚል በድፍረት ሲደነፋ ነበር፡፡ ሆቴሉ ከእነ ጭርሱ አገልግሎት እንዳያገኝ ሁሉ ሊያደርገው የሚችለውን የእነ አብይን ሴራ ለማስፈጸም ብሎ መስራቱ ሳያንስ እንደገና አሁንም ሊያውም በማይመለከተው ሰው ከልካዩ እኔ ነኝ እያለ ሲደነፋ ላየ ሒልተን ነው ወይስ የት ያሰኛል፡፡ ዓለም አቀፍ ተስተናጋጆችን የሚቀበል ሆቴል ጥበቃ ሰራተኞች የአብይ ኦዴፓ/ኦነግ ደህንነት ስለሆኑ በአለማስተዋል ይደነፋሉ፡፡

አብይም ሆነ ሌሎቹ በይፋ ይቅርታ ጠይቀው ራሳቸውን ካላስተካከሉ ይዘገያል እንጂ አይቀርላቸውም፡፡ መሠረታዊ ችግር ላያ ነው እያወራን ያለንው፡፡ አሁን የባዘኑ ይመስላሉ፡፡ በተረጋጋ ሁኔታ ሕዝብን ይቅርታ መጠየቅ ያባት ነው፡፡ የተስፋዬ ገብረአብ አምላኪዎች ተቆቱ ብሎ አዲሱ አረጋ ስንቴ ነው ይቅርታ የጠየቀው፡፡ አዲሱ አረጋ ታከለ ኡማን አዲስ አበባ ላይ ያመጣንው እኮ ለኦሮሞ እንዲሰራ ነው እመኑን ብቻ እያለ በሌላው ላይ ጥፋትን ለሚመኙ በደስታ ያስጨበጨበበትን ንግግሩን ይቅርታ ጠይቆናል፡፡ ሊያውም የቅርታ ብቻ አደለም ማብራሪያውም፡፡ እንግዲህ አዲሱ በግል ስለሚሰራው አደለም ያወራው አብይ የሚመራው ቡድን በአጠቃላይ እየሰራው ስላለው እንጂ፡፡ እነ ብርሀኑ ይሄን ነው ደግፉ የሚሉን፡፡

ቅዱስ እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ከተንኮለኞች ሴራ ይታደግ! አሜን!