June 14, 2019

Source: https://mereja.com/amharic/v2/124621
https://radiodownloaddw-a.akamaihd.net/Events/dwelle/dira/mp3/amh/0D343B76_2_dwdownload.mp3

Image result for ethiopian passport

DW : የኢትዮጵያውያን ፓስፖርት ፈላጊዎች 45 ቀናት መጠበቅ አለባቸው። ከዚህ ቀደም የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ማመልከቻ በቀረበ በሦስት ቀናት ውስጥ ፓስፖርት ይሰጥ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት እንዲራዘም ሆኗል። ረዥም ሰልፍ ወደ ሚታይበት የአዲስ አበባው የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ዋና መስሪያ ቤት ያቀኑ አገልግሎት ፈላጊዎች ለስርቆት መጋለጣቸውን ጭምር ይናገራሉ። በአስር ቅርንጫፎች አገልግሎት የሚሰጠው የኢሚግሬሽን ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ደቡብ ሱዳናውያን እና ኤርትራውያንን ጨምሮ ፓስፖርት ለማይገባቸው ሰዎች ጭምር እየተሰጠ እንደ ሆነ ገልጿል። Audio Player