
እኔ ሙስሊሞ ነኝ ይሄ 2992 አመታት በፊት
የአያት ቅድመ አያቶቼ የሰሩት ታሪክ ነው!!
ጥንታዊት ተድባበ ማርያም
*** *** ***
በደቡብ ወሎ በቀድሞው ቦረናና ሳይንት አውራጃ የምትገኘው ተድባበ ማርያም ቤተ ክርስትያን ከኢትዮጵያ አድባራት ቀደምቷ ናት፡፡ እድሜ ጠገብና ብዙ ዘመን የኖረች እጅግ ጥንታዊ መካነ ቅርስ ስትሆን አስራ ሁለት በር ባለው ተራራ ላይ ከሁሉም በሚቀድም ክብር የዛሬ 2992 ዓመት የተመሰረተች ታሪካዊ ስፍራ ናት፡፡
.
ከደሴ ከተማ ምዕራባዊ አቅጣጫ 200 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ ያልተነገሩ ድንቅ የኢትዮጵያ ታሪኮች በተሸሸጉበት የሳይንት ወረዳ የምትገኘው ታሪካዊ ስፍራ ከቀዳማዊ ምኒልክ ዘመን እስከ ዛሬ አያሌ ታሪኮችን ያስተናገደች ስፍራ ናት፡፡ እንደ አክሱም ጽዮን መስዋዕተ ኦሪት ከተሰዋባቸው ቀደምት ስፍራዎች አንዷ ናት፡፡ አክሱማውያን ነገሥታት ተድባበ ማርያም የሚሏትን ታላቅ ስፍራ የሚያስተዳድራት አለቃ ፓትረያሪክ ይባላል፡፡ ጣና ቂርቆስን ሊቀ ካህኑ፣ አክሱም ጽዮንን ንቡረ ዕዱ እንደሚሾምባት ሁሉ በተድባበ ማርያም የሚሾመው ፓትረያሪክ ነው፡፡ ተድባበ ማርያም የኢትዮጵያ የቅርስ ማዕከል ናት፡፡ ያላትን መዘርዘር መድከም ነው፡፡
.
የሀገር ቅርስ ጠብቃ ዘመን ያሻገረች ህያው ሙዚየም ናት፡፡ ነገሥታት ዘውዳቸውን አውልቀው የሰጧት፣ ካባቸውን የደረቡላት፣ ደስታቸውን በድንቅ ስጦታዎቻቸው የገለጹላት ስፍራ ናት፡፡ ዘመን ያስቆጠረችው ስፍራ ህንጻ ቤተ ክርስቲያን በየዘመናቱ በተነሱ ነገስታት ሲሰራ ሲፈርስ ኖሮ ዛሬ ከነሞገሱ የሚታየው ዘጠነኛው ህንጻ በንጉሥ ሚካኤል ዓሊ የተሰራው ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ የሳር ጣሪያዋ ደግሞ በ1955 ዓ.ም. በእቴጌ መነን መልካም ፍቃድና ገንዘብ ቆርቆሮ እንዲለብስ ተደርጓል፡፡33