ጄነራል አሳምነው ጽጌ ስለፋኖ ለኢትዮጲስ ጋዜጣ የሰጡት ቃል 
(#ምናባዊ ወግ 3 )
ኢትዮጲስ፦ በፋኖ ላይ የአብይና እና የአዴፓ አቋም ምንድነው?

ጄነራል አሳምነው ጽጌ፦ አዴፓ ድርጅት ነው፡፡ አብይ ግለሰብ ነው፡፡ ጥያቄውን ግልጽ አድርግልኝ፡፡
ኢትዮጲስ፦ በቅርቡ አዴፓ በአመራሮቹ በኩል የታጠቁ አካላት ወይም ፋኖዎች የአማራ ክልል ስጋት ላይ ወድቋል የሚል ዜና አሰራጭተዋል፡፡ በዚህ ላይ የእርሶ አቋም ምንድር ነው?
ጄኔራሌ አሳምነው ጽጌ፦ ሃቁ መታወቅ አለበት (ትንሽ ወዥንብር እሰማለው ሰሞኑን) ግን ግን ፋኖ ባንክ አልመዘበረም፡፡ ፋኖ እናት አልደፈረም፡፡ ፋኖ ወታደር አልገደለም፡፡ ፋኖ አስገድዶ ከህዝብ ግብር አልሰበሰበም፡፡ እውነቱ ይህ ነው፡፡ የአማራ አብራኩ ፋኖ ህዝብ የሚያውቀው የአማራው ዋስትና የኢትዮጵያም አለኝታ መሆኑን ነው፡፡ ስለዚህ ፋኖ ብሌናችን ነው፡፡ ማንሾካሾክ አይመቸንም፡፡ ልምምጥ የለም፡፡ አለቀ፡፡ ፋኖ ማለት እኔ ነኝ!! ለማታውቁት፡፡ ፋኖ ማለት አማራ ማለት ነው፡፡ 

ነፍጠኝነት የአማራ ስነልቦና ስሪቱ እንደሆነ ስለምረዳ፣ ፋኖ የክብር እና የኩራት ምንጫችን ነው፡፡ በዚህ የፋኖ የጀርባ አጥንት የአማራ ገበሬ እንደሆነ ማሳወቅ እፈልጋለው፡፡ ይህ መታወቅ አለበት፣ ግንዛቤ መኖር አለበት፡፡ 
ከአዴፓ አመራሮች ጋር እና ከፌደራል አመራሮች ጋር በፋኖ ላይ ያላቸውን ስጋት በተለያየ አጋጣሚዎች አሳውቀውኛል፡፡ የእኔ አቋም ሁሌም ጼኑ ነው፡፡ ፋኖ ማለት እኔ ነኝ፡፡ 

አማራውን በእንቁላል የምታታልሉበት ዘመን አልፏል፡፡ በስልጣን የምትሸውዱት አማራ ዛሬ የለም፡፡ በብር የምትገዙት አማራ ዛሬ የለም፡፡ በማዳበሪያችሁ የምትደልሉት አማራ አርሶ አደር የለም አሁን፡፡ አማራ ሆናችሁ ኑ፡፡ ወንድም ሆነን እየጠበቅናችሁ ነው፡፡ እህት ሆነን እየጠበቅናችሁ ነው፡፡ ኢህአዴግ እንደ ድርጅት ለበደለን በደል ይቅርታ አድርገናል፡፡ የእናንተ ቦታ አማራነት ነው፡፡ ኑ እኛ አማራ ነን፡፡ ኢትዮጵያን እንወዳለን፡፡ ለንግድ ሳይሆን ለዲሞክራሲ፡፡ ለአንድ ቡድን ብዝበዛ ሳይሆን ለህዝብ መንግስትነት፡፡ እና ለአገር፡፡ ለአገር ሉአላዊነት፡፡ እና አንድነት፡፡ ባጭሩ መሸበር አያስፈልግም፡፡

ኢትዮጲስ፦ አመሰግናለሁ
ጄነራል አሳምነው፦ እኔም ከልብ አመሰግናለሁ