June 18, 2019

Source: https://fanabc.com

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 11 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክር ቤቱ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላትን ሹመት አጸደቀ።

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 45ኛ መደበኛ ስብሰባ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት የቦርድ አባላት ሹመትን መርምሮ አፅድቋል።

በዚህም መሰረትም፦

  1. አቶ ታዜር ገብረእግዜአብሔር
  2. አቶ መስዑድ አደም
  3. ረዳት ፕሮፌሰር መኩሪያ መካሻ
  4. ዶክተር ታምራት ሀይሌ
  5. ወይዘሮ ህይወት ሃይሉ
  6. አቶ አብነት ዘርፉ
  7. አቶ በቀለ ሙለታ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ቦርድ አመራር ሆነው በሙሉ ድምፅ በምክር ቤቱ ተሹመዋል።

ሹመታቸው የፀደቀው የቦርድ አባላቱም በምክር ቤቱ ፊት ቀርበው ቃለ መሃላ ፈፅመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ኤጀንሲ ተጠርነቱ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሆኖ ከወራት በፊት በአዲስ አዋጅ እንደገና መቋቋሙ ይታወሳል።